በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በጃራ የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ 28 ሰዎች መጎዳታቸው፤ የተፈናቃዮቹ መጠለያም መውደሙ ተነገረ።
የተመድ እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ዘመቻ ማስፋፋቷ ለበርካቶች እልቂት ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል አስጠነቀቀ። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገራቸው ጋዛ ውስጥ ሃማስን ሙሉ ለሙሉ ማሸነፍ ይኖርባታል እያሉ ነው።
ወደ ሞስኮ የተጓዙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሰዓታት መነጋራቸው ተገለጸ።
የጀርመን ካቢኔ በሕገ-ወጥ ሥራ ላይ መሰማራትና ሕገወጥ የገንዘብ ውዝውርን ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ ሕግ ዛሬ አፀደቀ።