-ኢትዮጵያዉያን በሕገ-ወጥ መስመሮች ወደ ዉጪ እንዳይጓዙ በዤኔቭ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መከረ።ኤምባሲዉ ባለፈዉ ዕሁድ የአደን ባሕረ ሰላጤን ለማቋረጥ ሲሞክሩ 76 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በመሞታቸዉ ሐዘኑን ገልጧልም።--ሩዋንዳ ከዩናይትድ ስቴትስ የሚባረሩ 250 ስደተኞችን ልትቀበል ነዉ።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር «ሕገ ወጥ» እና «የመጥፎዎች መጥፎ» የሚላቸዉን ስደተኞች ወደ ሶስተኛ ሐገራት እያባረረ ነዉ።--የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር የቢኒያሚን ኔታንያሁ መንግሥት ጋዛ ዉስጥ የከፈተዉን ጦርነት ለማጠናከርና ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመግዛት አቅዷል መባሉን የተለያዩ የእስራኤል የቀድሞ ባለሥልጣናት ተቃወሙት።