የነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
ከሶማሊያ ተነስተው ወደ የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 7 ኢትዮጵያውያን በረሀብ እና በውኃ ጥም መሞታቸውን የተመ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM አስታወቀ።
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስን ያነጋገሩት የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብጽ የሱዳንን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚደግፍ ጽኑ አቋም እንዳላት አረጋገጡ።
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለዩክሬን ከትራምፕ ጋር እንደሚነጋገሩ አረጋገጡ። ጉባኤው መቼና የት እንደሚካሄድ፣ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ መሳተፍ አለመሳተፋቸውም አልተነገረም።