-የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደርስበትን እልቂት ለመግታት በሥልጣን ላይ ያለዉን መንግስት በሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሕዝባዊ ትግል መቀየር እንዳለበት የሐገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ጥሪ አደረገ።--የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት መጀመሩን በይፋ አረጋገጠ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሕጋዊ ፓርቲነት ያገደዉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶብረፅዮን ገብረ መድሕን የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥትን ወቅሰዋል።--እስራኤል ያወደመቻትን የጋዛ ሰርጥ ርዕሠ-ከተማ ጋዛ ከተማን በጦር ሐይል ለመቆጣጠር መወሰኗ ከዉጪም ከዉስጥም ዉገዝትና ተቃዉሞ ገጥሞታል።