የሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
ኢትዮጵያውያን የሚያመዝኑባቸውን ስደተኞች የጫነች ጀልባ በአደን ባህረ ሰላጤ ሰጥማ ቢያንስ 68 ስደተኞች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህጻሩ IOM አስታወቀ። የየመን ባለሥልጣናት በበኩላቸው በአደጋው ቢያንስ 76 ስደተኞች ሞተዋል ብለዋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች በእርዳታ እጦት ሠዎች እየሞቱ ነው፣ አብዛኛዎቹም ለልመና ወጥተዋል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናገሩ ።
ጋዛ ውስጥ የታገቱት ሰዎች ይዞታ ዋነኛ ዓለም አቀፍ አጀንዳ መሆን አለበት ስትል እስራኤል አሳሰበች።