የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሐምሌ 15 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ «አደገኛ የሰዉ አዘዋዋሪ ወንጀለኛ» ያለዉን 17 አባላት ያሉት መረብን መበጣጠሱን አስታወቀ።---የዓለም የረሐብተኞች ቁጥር አምና ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት መቀነሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የረሐብተኛዉ ቁጥር ቢቀንስም የዓየር ንብረት መዛባትና የንግድ መደናቀፍ የረሐብተኛዉን ቁጥር እንደገና ሊያንረዉ ይችላል።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የገጠሙት ጦርነት የባብ ኤል መንደብን መስመርም አዘግቷል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ተፋላሚዎች የሲቢል ተቋማትን እንዳይመቱ ተማፅነዋል።የአሜሪካ ፕሬዝደንት ግን የኢራንን ድልድዮችና የነዳጅ ተቋማት ለማዉደም እየዛቱ ነዉ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
    አርስተ ዜና፤ ኢሕአፓ በትግራይ አዲስ የጦርነት ሥጋት ማንዣበቡን በመግለፅ ጥሪ አቀረበ። ፓርቲው መንግሥት በሚያስተዳድራቸው መገናኛ ብዙኃን የሚካሄድ ያለው "የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና የሕዝብን ሥነ-ልቦና ለጦርነት የማዘጋጀት ሙከራ" ከአራት ዓመታት በፊት በትግራይ ጦርነት ዋዜማ ከታየው ሂደት ጋር አንድ አይነት ነው"ብሏል።- የአራት ቀናት አፍሪቃ ሃገራት ጉብኝታቸዉን ከሞሪታንያ የጀመሩት የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሃን ቫዴፉል የሞሪታንያ ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ናይጀርያ ገብተዋል። ሚኒስትሩ አገራቸዉ እና ሞሪታኒያ በንግድ፣ በኃይል ቀርቦትና በደኅንነት ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠነክሩ ገልፀዋል።
    11 min
  • የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ከሱዳኑ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጋር በምታካሂደው ጦርነት ኬሚካዊ የጦር መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ አውላለች ባለቻት በሱዳን ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ አዲስ ማዕቀብ ጣለች።ለክሱ ያቀረበችው ማስረጃ ግን የለም ተብሏል።
    ዛሬ የተመረጡት አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሀም መንግሥት እንዲመሰርቱ በንጉሥ ቻርልስ ሣልሳዊ ተጠየቁ። የቀድሞ የግሬተር ማንቼስተር ከንቲባ የ56 ዓመቱ በርንሀም ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት የሌበር ፓርቲ መሪነት ከተመረጡ ከ3 ቀናት በኋላ ነው።
    የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ የስፔን ቡድን ዛሬ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና አቀባበል ተደርገለት።
    12 min
  • DW Amharic የሐምሌ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በሶማሌ ክልል ቀብሪ በያሕ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ። ለ2019 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 704 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ። በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ምዕራባዊ ክፍሎች፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በጋምቤላ ክልል በተወሰኑ አካባቢዎች በሚጥል ከባድ ዝናብ ምክንያት የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስጠነቀቀ። የታንዛኒያ ሰንደቅ የሚያውለበልብ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከየመን የባሕር ዳርቻ በሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ታገተ። አሜሪካ ሁለት ወታደሮቿ በዮርዳኖስ ከተገደሉ በኋላ ኢራንን “ለመቅጣት” አዲስ ዙር የለሊት የአየር ላይ ድብደባ ፈጸመች።
    8 min
  • የሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ-ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና ፤በአዲስ አበባ ከተማ ህወሓትን የሚቃወም ሰልፍ መካሄዱን፤ኢራን 'የአሜሪካ ጥቃቶች ከቀጠሉ ምንም አይነት የፖለቲካ ድንበር ደህንነቱ የተጠበቀ አይሆንም' ስትል ማስጠንቀቋን፣የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለማግኘት ወደ ዋሽንግተን ማቅናታቸውን፤በጀርመን ከፍተኛ የሽብር ስጋት መኖሩን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር መግለፁን፣ዩክሬይን በሁለት የሩስያ ግዛቶች ሌሊቱን ለዛሬ አጥቢያ ፈጸመችው በተባለ የድሮን ጥቃቶች 9 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሩስያ ባለስላጣናት ማስታወቃቸውን እንዲሁም ህንድ የመጀመሪያውን የግል ሮኬት ወደ ህዋ ማምጠቋን አካቷል።
    11 min
  • የሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና፤ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብደል ፋታኅ አል ቡርኻን በአስመራ መገናኘታቸውን፣ሶማሊያ በየኮቪድ-19 ሰበብ የ250 ሚሊዮን ዶላር ማጭበርበር የተከሰሰ ቁልፍ ተጠርጣሪን ለአሜሪካ አሳልፋ መስጠቷን፣የኢራን አብዮታዊ ዘብ በዮርዳኖስ የአሜሪካን አውሮፕላኖችን በሚሳኤልና በድሮን መምታቱን፣ አንዲ ቡርንኻም በብሪታኒያ በሥልጣን ላይ የሚገኘው ሊበር ፓርቲ መሪ ሆነው መመረጣቸውን እና ቻይና አሜሪካ በጋዜጠኞች የቆይታ ጊዜ ላይ በጣለችው ገደብ ላይ 'የአፀፋ እርምጃዎችን' እንደምትወስድ ማስጠንቀቋን አካቷል።
    12 min
  • የሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ ስለተጀመረው አገራዊ ምክክር የፓርቲዎች ትችት እና ድጋፍ፤ ሙዋንጋ ፥ ዛምቤዚ ባህር ሰጥመዋል የተባሉ ኢትዮጵያዉያን በሕይወት ተገኙ፤ ዋሽንግቶን፥ ዩናይትድ ስቴትስ በኢቦላ ከተጠቃችው ኮንጎ የሚመጡ ዜጎቿን ወደ አገር መግባት ከለከለች፤ ኪዬቭ፥ አዲስ ጠቅላይ ሚንሥትት ተሾሙ፥ መከላከያ ሚንሥትሩ ተሻሩ፤ቴሕራን፥ ኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ስትደበድባት የባህረ ሠላጤው አገራት ላይ ጥቃቷን አጠናከረች፤ ሣንዓ፥ የሑቲ ዓማጺያን የሣዑዲ ዓረቢያን እንደሚደበድቡ ዛቱ
    10 min
  • የሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሯል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ « ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፣ ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ምክክሩ ፍሬያማ ይሆናል በማለት ለጉባኤተኞቹ ጥሪ አቅርበዋል።
    ወደቦትስዋና ለመሻገር የሞከሩ 10 ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩባት ታንኳ ተገልብጣ ሳይሰጥሙ እንዳልቀረ የዛምብያ ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። በታንኳዋ ተሳፍረው ከነበሩት 15 ኢትዮጵያውያን አስሩ ሰጥመዋል ተብሎ እንደሚታመን የተናገረው ፖሊስ ሦስት ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጿል። ከመካከላቸው በህይወት የተረፉትን ሁለቱን ፖሊስ አስሯቸዋል።
    የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ጥቃትና የአጸፋ ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 7 ቀን 2028 ዓ.ም ማክሰኞ
    አርስተ ዜና-የአሜሪካ ጦር ለሦስተኛ ተከታታይ ምሽት በኢራን ኢላማዎች ላይ ጥቃቶችን ማካሄዱን አስታወቀ። የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ ፤ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ሁለት ከፍተኛ ነዳጅ መርከቦችን መምታቱን እና ከጉዞ ማሰናከሉን አስታውቋል።-ከስድስት ዓመት በላይ ከኦሮሚያ ክልልና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን በመጠለያ ጣቢያና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና ሥጋት መጋለጣቸውን ተናገሩ።-አውሮጳ ህብረት በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ የሚዉለዉን የገንዘብ ድጋፍ ለመቀነስ በሱዳን የወርቅ ንግድ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ።
    13 min
  • የሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ በማስቆም ሕገ መንግስታዊ ግዴታውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ። የየመን ሑቲ ታጣቂዎች ሳውዲ ዓረብያ በሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ«ፈጸመችው» ላሉት ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስጠነቀቁ። አሜሪካ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ሰርጥ «እየፈጸመው ነው» ላለችው ማስተጓጎል ያስታገሰ ያለችውን ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች። ኢራን በበኩሏ በዮርዳኖስ፣ ባሕረይና ኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ደብድባለች።
    13 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…