የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የሱዳን ፍርድ ቤት መሐመድ ሐምዳን ዳግሎን ጨምሮ 16 የፈጥኖ ደራሹ ኃይል RSF አመራር በሌሉበት የሞት ቅጣት ፈረደ።
    • ደቡብ አፍሪካ ሶስት የቤተሰቡን አባላት በመግደል ሸሽቶ ወደ ሐገሯ ገብቶ የነበረውን ብሪታንያዊ አሳልፋ ልትሰጥ ነው።
    • የኢራን አብዮታዊ ዘብ የሆርሙዝ ሰርጥ መዝጋቱን አስታወቀ።
    • የእስራኤል ጦር ኃይል በጋዛ ሰርጥ ባደረሳቸው ጥቃቶች አንዲት የ9 ዓመት ሴት ልጅን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታወቁ።
    • የቀድሞው የቃጣር መሪ ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ። 74 ዓመታቸው ነበር ።
    9 min
  • DW Amharic የሐምሌ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአገሪቱ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመች። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አሜሪካ ያዘጋጀችውን ምክረ-ሐሳብ የሚቀበለው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከተቆጣጠራቸው ከተሞች ለቅቆ ሲወጣ እንደሆነ ቅድመ-ሁኔታ አስቀመጠ። የናይጄሪያ ጦር በዛምፋራ ከ300 በላይ ታጣቂዎች ገደለ ተባለ። የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞሽታባ ኻሜኒ አገራቸው የአባታቸውን ገዳዮች መበቀሏ “አይቀሬ” እንደሆነ ዛቱ። የአሜሪካው ፕሬዝደንት በኢራን ላይ ያነጣጠሩ 1,000 ሚሳይሎች መጠመዳቸውን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 29 ቆሰሉ።
    11 min
  • የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢኩዋቶርያል ጊኒ የተጠረዙ ከኢትጵዮያ፣ከአንጎላ እና ከሞሪቴንያ መሆናቸው የተገለፀ 17 ስደተኞች በተያዙበት ሆቴል ውስጥ በኤቦላ እንደተያዘ የሚጠረጠር ቢያንስ አንድ ሰው ተገልሎ እንደሚገኝ የተጠራዦቹ ጠበቆች ተናገሩ።
    ማላዊ 38 ሺህ ዜጎቿን በአንድ ወር ውስጥ ከደቡብ አፍሪቃ ወደ ሀገራቸው መመለሷን ዛሬ አስታውቃለች። ስድስት የማላዊ ዜጎች መንገድ ላይ ታመው ሞተዋል።
    የጀርመን የእግር ኳስ ፌደሬሽን በምህጻሩ DFB ፕሬዝዳንት እና ምክትላቸው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን አስልጣኝነት ከታጩት ከዩርገን ክሎፕ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ወደ ኒውዮርክ ተጓዙ።
    11 min
  • የሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ናሜይ፥ ሩስያ እና የሣኅል ቀጠና አገራት ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ሊያጠናክሩ ነው ፤ አንካራ፥ የኔቶ ጉባኤ በተሳታፊዎች ስምምነት ተጠናቀቀ፤ቤርሊን፥ ራኄ መንግሥት ፍሪደሪሽ ሜርስ ትናንት የተጠናቀቀው ኔቶ ጉባኤ ከጠበቁት በላይ መኾኑን ተናገሩ፤ ቴሕራን፥ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ጥቃት እየተሰናዘሩ ነው፤ ማሽሐድ፥የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ፤ ሞሮኮ እና ፈረንሣይ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ፍልሚያ
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓም ረቡዕ
    አርስተ ዜና፤ የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስና ወታደራዊ ኃይል በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ላይ ባደረጉት ከፍተኛ ዘመቻ ከ200 በላይ ሰዎችን አሰሩ። በደቡብ አፍሪቃ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል ህጋዊ ወረቅት የሌላቸዉ ስለመያዝ አለመያዛቸዉ እስካሁን የወጣ ግልፅ መረጃ የለም።-የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኔቶ ስብሰባ አንካራ ተገኝተዋል። ትራምፕ ድርጅቱ ባሳየዉን ወታደራዊ ኤግዚቢሽን የተደሰቱ አይመስልም። የአውሮጳ ህብረት ሀገራት ኔቶን ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረትና የኢራን ጦርነት ለመቀላቀል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ትራምፕ በተደጋጋሚ ተችተዋል።
    11 min
  • የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ ጠ/ሚ ዐቢይ ስለ ሕገ መንግሥቱ ተናገሩ፤ ናይሮቢ፥ የኬንያ ፖሊስ የመታሰቢያ ሰልፍ ከለከለ፤ ​​​​​​​ኪንሻሳ፥ የኢቦላ ወረርሺኝ በኮንጎ መዛመቱን እንደቀጠለ ነው፤ ደማስቆስ፥ ሶሪያ ውስጥ በፈረንሣይ ፕሬዚደንት ጉብኝት ወቅት በደረሰ ፍንዳታ 18 ሰዎች ቆሰሉ፤ ፓሪስ፥ ፈረንሣይ እና ሶሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ፤ አትላንታ፥ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት የመጨረሺያ ግጥሚያዎች
    12 min
  • DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት የ15 ዓመት አዳጊዎችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን እያፈኑ በግዳጅ ለውትድርና በመመልመል ላይ እንደሚገኙ ሒውማን ራይት ዎች ወነጀለ።
    በሱዳን እየተካሔደ በሚገኘው ጦርነት በስድስት ወራት ብቻ 330 ሕጻናት መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ሐማስ የጋዛን መንግሥታዊ መዋቅር መፍረሱን አስታወቀ። የዩክሬን ጦር ኦምስክ በተባለ ግዙፉ የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት ፈጸመ። ለጀርመን ለሚቀጥለው ዓመት የ555.4 ቢሊዮን ዩሮ ረቂቅ በጀት ጸደቀ። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር ከሥምምነት ላይ ካልደረሰች አገራቸው የጀመረችውን ጦርነት "እንጨርሰዋለን" ሲሉ ዛቱ
    13 min
  • DW Amharic-የሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና በቀይ ባሕር ትቀዝፍ የነበረች አንዲት ዕቃ ጫኝ መርከብ በየመን ሁዴይዳ የባሕር ክልል አካባቢ ጥቃት ተፈፀመባት መባሉን፣ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በሂዝቦላህ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ አጠናክራ እንደምትቀጥል መግለጿን፣በእስራኤል እስር ቤት ውስጥ የሚገኙት የጋዛ ሆስፒታል ዳይሬክተር ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል መባሉን፣ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአያቶላህ አሊ ካማኔይ የሀዘን ሥነ ሥርዓት ላይ ልጆቻቸው እና ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናት መገኘታቸውን እንዲሁም ትራምፕ በአሜሪካ 250ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ባደረጉት ንግግር የሀገር ፍቅርን ከፓርቲ ፖለቲካ ጋር ቀላቅለዋል በሚል መተቸታቸውን አካቷል።
    8 min
  • የሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና ፤ የትግራይ ክልል አሁን ያለበት ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለፁን፣የአውሮፓ እና የአሜሪካ መሪዎች ስደተኞችን ለመጠበቅ እና ለማዋሃድ የበለጠ እንዲሰሩ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳሥ ማሳሰባቸውን፣ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊካሜኒ ብሄራዊ የሽኝት ሥነ ስርዓት ዛሬ በይፋ መጀመሯን፣ጀርመን፤ ቤጂንግ የሩሲያ ወታደሮችን ማሰልጠኗን የሚያሳዩ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ቻይናን ማስጠንቀቋን፣አማራጭ ለጀርመን የተባለው መጤ ጠል ፓርቲ ዛሬ መሪዎቹን መምረጡን እንዲሁም ዶናልድ ትራምፕ ለ11 ተከሳሾች ይቅርታ ማድረጋቸውን የሚያስቃኙ ዜናዎች ተካተዋል።
    11 min
  • የሰኔ 26 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዘይሴ ወረዳ የመንግሥት ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸዉን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።---የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አ,ያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ አስከሬን የሽኝት ሥርዓት ዛሬ ቴሕራን ዉስጥ ተጀመረ።ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ የተገደሉት ኻምኔይ ኢራንን ለ37 ዓመት መርተዋል።86 ዓመታቸዉ ነበር።--ሐሙስ ይቀበራሉ።-የጀርመን የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዩሊያን ናግልስ ማን በከፍተኛ ግፊት ሥልጣኑን ለቀቀ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…