የግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
አንድ የዕቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ዛሬ በሱዳንዋ ምዕራብ ዳርፉር ግዛት ውስጥ በሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በቦምብ መመታቱን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ።
ጋዛ ሰርጥ ውስጥ እርዳታ የሚያከፋፈልባቸው ማዕከላት ለጊዜው መዘጋታቸውን በዩናይትድ ስቴትስና በእስራኤል የሚደገፈው የጋዛ ሰብዓዊ ድርጅት የተባለው ቡድን አስታወቀ።
የአውሮፓ ኅብረት ዋነኛ የንግድ ተደራዳሪ ማሮስ ስፌሶቪክ ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ በብረታ ብረቶች ላይ በእጥፍ የታሪፍ ጭማሪ ማድረጓ ድርድሩን የሚያግዝ እንደማይሆን ተናግረዋል።