የደርግ ሥርዓት ከኢትዮጵያ የመንግሥት ሥልጣን ከተወገደ ዛሬ 34 ዓመቱን ደፈነ። ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በብሔራዊ በዓልነት ይታሰብ የነበረው ግንቦት 20 በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች መደበኛ የሥራ ቀን ሆኖ ሲያልፍ ትግራይ ክልል ግን በደመቀ ሥርዓት ተከብሯል።
ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በሱዳን ጦር ኃይል የተያዙ አካባቢዎች ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙ ተዘገበ።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቁ።
የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአብዛኛው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናትን ጨምሮ ወደ 300 ገደማ ህሙማን ላይ በደል በፈጸመ የቀዶ ህክምና ባለሙያ ላይ የ20 ዓመት እስራት ፈረደ።