አርስተ ዜና
የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ፍሬድሪክ ሜርስ ስራኤል በጋዛ እየፈፀመች ያለዉ ድርጊት «ትክክል ያልሆነ» ሲሉ ወቀሱ። በሌላ በኩል ጀርመንን ጨምሮ ቁልፍ ምዕራባዉያን የዩክሪን ደጋፊዎች ለዩክሪን በሚልኩት የጦር መሳርያ ላይ የተጣለ ገደብን አነሱ።--በእነአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ የተሰኘ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ግዚያዊ የምዝገባ ፍቃድ አገኘ።--በጦርነት በተመሰቃቀለችዉ ሱዳን በኮሌራ በሽታ የተያዘዉ ሰዉ ቁጥር መጨመሩን የጤና ጥበቃ ሚ/ር አስታወቀ።--የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የፊንላንድ የአየር ክልልን ጥሰዋል ከተባለ በኋላ ፊንላንድ የሩሲያን አምባሳደር ለጥያቄ ጠራች።