ከአዲስ አበባና ከሌሎች የመሐል ኢትዮጵያ ግዛቶች ሸቀጦች ጭነዉ ወደ ትግራይ ይጓዙ የነበሩ የጭነት መኪኖች አፋርና አማራ ክልል በሚገኙ የፍተሻ ጣቢያዎች መታገዳቸዉን ሾፌሮች አስታወቁ።---የአሜሪካዉ አዉሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ኢንዶኔዢያና ኢትዮጵያ ዉስጥ በደረሱ አደጋዎች ሰበብ የተመሠረተበት ክስ ሊነሳለት ነዉ።ክሱ የሚነሳዉ ቦይንግ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል በመስማማቱ ነዉ።-እስራኤል ለጋዛ ሕዝብ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይደርስ ማገዷን እንድታቆም የሚደረግባት ግፊት እንደቀጠለ ነዉ።የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ግን መንግሥታቸዉ ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የአይሁዳዊ የእስራኤል መንግሥት እንደሚመሠርት ዝተዋል።