የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    የኬንያ የሰራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ወጣቶችን ለሩስያ በወታደርነት በመመልመል እንደሚጠረጠሩ ተገለጸ። በቀጠር በአንድ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ በደረሰ ፍንዳታ 13 ሰዎች ሲሞቱ በ 54 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቀጠር የሐገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በዮናይትድ ስቴትስና ኢራን መካከል በስዊዘርላንድ ሲካሄድ የነበረ ንግግር በጥሩ መንፈስ መጠናቀቁን የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውንና ከሌበር ፓርቲ መሪነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚለቁ አስታወቁ።
    10 min
  • የሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ገዡ ፓርቲ ብልፅግና 90 በመቶ ድምፅ ማግኘቱን ምርጫ ቦርድ መግለጹን፣በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ እና ገለልተኛ ተቋም ሆኖ መስራቱን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ መናገራቸውን፣በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ያለስጋት እንዲሳተፉ ሁሉን አቀፍ ርምጃ ተወስዷል ሲል የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ማለቱን እና በምርጫ ወቅት ጥቃቶች መፈፀማቸውን መጠቆሙን እንዲሁም ገዥው ፓርቲ ብልፅግና በቀጣይ አምስት የስልጣን አመታት የነበሩ ችግሮችን እንዲቀርፍ ነዋሪዎች መጠየቃቸውን አካቷል። # ምርጫ2018 #EthiopiaElection2026
    7 min
  • የሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ ጉዳይ ልዩ መርማሪ በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተባባሰ መምጣቱን አስታወቁ።
    • በእስር ላይ የነበረችው ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ መፈታቷን ቤተሰቦቿ ለዶቼ ተናገሩ።
    • በምስራቃዊ ሊቢያ የባህር ዳርቻ የአንድ ህጻን ሴት ልጅን ጨምሮ በትንሹ የ15 ፍልሰተኞች አስከሬን ተገኘ።
    • አፍሪካ እና የካሪቢያን ሀገራት መሪዎች ጥቁሮችን ለባርነት የዳረጉ ያሏቸውን ሃገራት ካሳ እንዲከፍሉ ጠየቁ ።
    • ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን በድጋሚ ዘጋች።
    • አውሮጳን እያናወጠ የሚገኘው አስከፊ የሙቀት ማዕበል በጀርመን ፣ፈረንሳይ እና ጣልያን ብርቱ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተነገረ።
    11 min
  • የሰኔ 12፣ ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በትግራይ ክልል ለወታደራዊ ስልጠና የሚደረገው የአፈሳ ዘመቻ ብርቱ ትችት እና ተቃዉሞ መቀስቀሱ ተዘገበ ።
    • በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዛሬ ዓርብ አስጠነቀቀ።
    • እስራኤል እና የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ቀደም ሲል አድርገው የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማደስ መስማማታቸው ተገለጸ።
    • የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ የኅብረቱን ጥቅሞች ለማስከበር ከሩስያ ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ለመጀመር ያቀረቡት ሐሳብ ሳይሳካ ቀረ።
    12 min
  • የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና
    -ዩናይትድ ስቴትስ «አክራሪ» ባለቻቸዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ያነጣጠረ የቪዛ እገዳ ጣለች። ዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ እገዳዉን የጣለችዉ / በትግራይ ክልል ሠላም ለማስፈን የተደረገዉን ስምምነት በሚጥሱና ከሚጥሱ ወገኖች ጋር በሚተባበሩ ሰዎች ላይመሆኑን አስታውቃለች። -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ግንቦት በተደረገዉ ምርጫ ሒደት ቅሬታ ከቀረበባቸዉ 128 የምርጫ ክልሎች ለ85ቱ ዉሳኔ መስጠቱን ዐሳወቀ።
    -በኤልኒኞ ምክንያት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ 22 ሀገራት ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸውን FAO እና የWFP ዛሬ በጋራ አሰሳቡ።
    11 min
  • የሰኔ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያስገነባችዉ ግድብ ግብፅን ለብዙ ችግሮች አጋልጧል አሉ።ትራምፕ የግብፅ አቻቸዉን ዛሬ ሲያነጋግሩ እንዳሉት መስተዳድራቸዉ ሁለቱን ሐገራት ለማግባባት እንደሚጥር አስታዉቀዋልም።---በ13 ሐገራት ወይም ግዛቶች የሚኖር በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ካላገኘ ለአስከፊ ረሐብ እንደሚጋለጥ የተባበሩት መንግሥታት ሁለት ድርጅቶች አስታወቁ።ድርጅቶቹ እንደሚሉት ሱዳን፣ ሶማሊያና ጋዛን ጨምሮ ለችግር የተጋለጡ 266 ሚሊዮን ሰዎች በቂ ርዳታ አያገኙም።---የቡድን 7 አባል ሐገራት መሪዎች በማደግ ላይ ባሉ ሐገራት ላይ ያለዉን ዕዳ ለማቃለል ቃል ገቡ።
    11 min
  • የሰኔ 9 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በዚምባብዌ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከባቡር ጋር በመላተሙ ቢያንስ 9 ሰዎች ሲሞቱ 25 መቁሰላቸውን የሐገሪቱ የሐገሪቱ ባለስልጣናት አሳወቁ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐገራቸው ከአሜሪካ ጋር የመጨረሻው የሰላም ስምምነት በመጨው አርብ በስዊትዘርላንድ እንደሚፈረም አረጋገጡ።ዩክሬን በሞስኮ አቅራቢያ የሚገኘውን የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ማጋየቷ ተሰማ። ጀርመን ወደ 30 የሚሆኑ የአፍጋኒስታን ዜጎች ከሐገር ማባረሯን አሳወቀች።
    13 min
  • DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማጓጓዣ አውቶቡስ 170 ሜትር ርዝመት ያለው ገደል ውስጥ በመውደቁ የ31 ሰዎች ሲሞቱ 30 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደረሰባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቢሾፍቱ አቅራቢያ እየተገነባ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ምክንያት “የሚጎዳ አርሶ አደር” እንደማይኖር ቃል ገቡ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ በሱዳን ጦርነት የድሮን አጠቃቀም ላይ የታየውን “ከፍተኛ ጭማሪ” አወገዙ። ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን የገጠሙትን ጦርነት ለማብቃት ከሥምምነት መድረሳቸውን አሳወቁ። ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ በሚሳይሎች በፈጸመችው ጥቃት11 ሰዎች ተገደሉ።
    13 min
  • የሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት አብዲራሕማን ሞሐመድ አብዱላሒ "ታሪካዊ" የተባለለትን ጉብኝት እውቅና በሰጠቻቸው ሀገር እስራኤል እያደረጉ ነው።
    በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻ ከ 700 በላይ ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
    የእስራኤል ጦር ዛሬ የሂዝቦላህ ቡድንን ለማጥቃት የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ክፍልን ከአየር ደበደበ። ቡድኑ አስቀድሞ ዛሬ ጠዋት በሰሜናዊ እስራኤል የድሮን ጥቃት ፈፅሟል።
    የኢራን ዋና ተደራዳሪ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ በዚህ አይነት ሁኔታ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሰላም ድርድሩን መቀጠል ፋይዳ እንደማይኖረው ተናገሩ።
    8 min
  • የሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የኤርትራው የማስታወቂያ ሚንስትር የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ በተዛባ መረጃ ላይ የተመሰረተ ፕሮፖጋንዳ ያሰራጫል ሲሉ ከሰሱ ።
    • በኢራን እየተካሄደ ያለው ጦርነት የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋን በመናርና የአቅርቦት እጥረትን በመፍጠር በአፍሪካ አየር መንገዶች ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየደቀነ መሆኑን የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር (AFRAA) አስጠነቀቀ።
    • ዩጋንዳ በኤቦላ ወረርሽኝ ምክንያት በአሜሪካ እና በሌሎች ሀገራት የተጣለባትን የአየር ጉዞ እገዳ «ኢ-ፍትሐዊ» ስትል ኮነነች።
    • የኒጀር ወታደራዊ ሁንታ ግብረ-ሰዶማዊነትን በወንጀል የሚቀጣ አዲስ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ማውጣቱን አስታወቀ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…