የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአፍሪቃ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ መቀለ መጓዙ ተሰማ። የቡድኑ መሪ የጉዟቸው ዓላማ ሁኔታዎች እንዳይባባሱ አስቀድሞ ለማርገብ ነው ብለዋል።
    የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጁ ነው መባሉን ውድቅ ማድረጋቸው ተዘገበ።
    «ላ ክሯ» ለተሰኘ ጋዜጣ የምትዘግብ ፈረንሳዊት ጋዜጠኛ ከኢትዮጵያ መባረሯን ድርጅቱ አመለከተ።
    የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን አሾልካ አወጣች ያሉት የስምምነት በጽሑፍ ያለውን ውል የሚወክል አይደለም አሉ። የኢራን ባለሥልጣናት በበኩላቸው ጣላቶቻችን ያሏቸው አሜሪካን እና እስራኤል ከኃይል በቀር የድርድር ቋንቋ አይገባቸውም ብለዋል።
    12 min
  • የሐሙስ ሰኔ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቐለ፥ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን ዛሬ መቐለ ከተማ ዉስጥ ተቀብለው አነጋገሩ፤ አ.አ፥ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ለፕላን-በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመራ፤ ጂዳ፥ ሣዑዲ ዓረቢያ ታስረው የነበሩ 1,655 ኢትዮጵያውያን ምሕረት አገኙ፤ የአሜሪካ ጦር በሁለተኛው ቀን ኢራን ውስጥ በርካታ ኢላማዎችን እየመታ መሆኑን ዐሳወቀ፤ ኬፕታውን፥ የኬፕ ታውን ማራቶን ከዓለማችን ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ ኾነ፤ ሜክሲኮ ሲቲ፥ የዓለም እግር ኳስ ጨዋታ በደቡብ አፍሪቃ እና በሜክሲኮ መካከል ዛሬ ማታ ይከፈታል
    12 min
  • የሰኔ 3 ቀን፣ 2018 የዓለም ዜና
    -ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክና ዩጋንዳ ዉስጥ የተሰራጨዉ የኢቦላ ተሕዋሲ የያዛቸዉ ሰዎች ቁጥር 620 ደረሰ።ተሕዋሲዉ 120 ያክል ሰዎች መግደሉ ተረጋግጧል።ሶስት የኮንጎ ቤተ-ምርመራዎች ተሕዋሲዉን መመርመሪያ መሳሪያና ንጥረ-ነገር አልቆባቸዋል።---ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን እንዳዲስ መደባደብና መዛዛት ይዘዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የኢራን ወታደራዊ ተቋማት ያላቸዉን ሥፍራዎች ሲደበድብ፣ ኢራን ባፀፋዉ ከባሕሬን እስከ ዮርዳኖስ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሠፈሮችን ደብድባለች።----ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገባ የተከለከለዉ ሶማሊያዊ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ግጥሚያ ዳኛ ሞቃዲሾ ሲመለስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
    አርስተ ዜና--በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተፈናቃዮች ልዩ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በአማራ ክልል ዛሬ ተከናወነ። ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በነበሩ የፀጥታ ችግር ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸዉ እንዲመለሱ ጠይቀዋል።-በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ተባብሶ እንደቀጠለ የተገለፀውን ውጥረት በተመለከተ፣ የፕሪቶሪያውን ግጭት በዘላቂነት የማቆም የሰላሞ ስምምነት በዋነኛነት ከመራው የአፍሪቃ ኅብረት በኩል እስካሁን የወጣ መግለጫም ይሁን የተሰጠ አስተያያት የለም።-የዓለም ዋንጫ ጨዋታን ለመምራት ለሀገሩ የመጀመሪያው ለመሆን የተዘጋጀው ሶማሊያዊ ዳኛ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ተከለከለ።
    13 min
  • የሰኞ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ደቡብ አፍሪቃ በሚገኙ ስደተኞች ላይ ከሕግ በላይ ሆነው እርምጃ የሚወስዱትንሰዎች ባለሥልጣናቶቻቸውእንደማይታገሱ አሳሰቡ ።
    ኢራን እስራኤልን ትናንትናና ዛሬ ስትደበድ እሥራኤልም በአጸፋው ኢራንን ዛሬ መታለች ። ትናንት ወደ እሥራኤል ሮኬቶችን በተመተኮስ ማጥቃት የጀመረችው ኢራን 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመከላከል ዘመቻውን እንደምታቆም አስታውቃለች። ከእሁዱ የኢራን ጥቃት በኋላ የእሥራኤል ጦር ዛሬ (መጠነ ሰፊ) ያለውን ጥቃት በኢራን ላይ መፈጸሙን ገልጿል።
    ማልታ አቅራቢያ በሰጠመች ጀልባ ውስጥ የነበሩ ቢያንስ 11 ስደተኞች ሞቱ። ወደ 50 የሚሆኑ ደግሞ ተረፉ።
    11 min
  • የግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የማዕከላይ አፍሪካ ሪፐብሊክ መንግስት ከአሜሪካ የሚጠረዙ ስደተኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ መስማማቱን ከሐገሪቱ የወጡ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች አረጋገጡ። ዩናይትድስቴትስና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ዛሬ 100 ቀናትን ደፍኗል። ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ባንኮች ታግዶ የሚገኘውን የኢራን ሐብት፤ በኢራን የሚሳይልና የድሮን ጥቃት ለደረሰባቸው የባህረ ሰላጤ ሀገራት እንዲውል ማቀዷን አስታወቀች።
    10 min
  • DW Amharic-የቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና ፣የኢትዮጵያ አየር ሃይል በትግራይ ክልል ሸራሮ ከተማ አቅራቢያ አካሄደው በተባለው የድሮን ጥቃት ጉዳት ደረሰ መባሉን።ናይጄሪያ እና ጋና ዜጎቻቸው ደቡብ አፍሪካን ለቀው እንዲወጡ ሀሳብ ማቅረባቸውን፣ኩዌት፤ አዲሱ የኢራን ጥቃት 'አደጋ የሚያባብስ ' መሆኑን መግለጿን።በጀርመን በፖለቲካዊ መነሻ የሚፈጸም ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል መባሉን፣የሮማው ሊቃነ ጳጳስ በዓለም ላይ ዋልታረገጥነ አስተሳሰብ እንዲያበቃ ጥሪ ማቅረባቸውን እንዲሁም ኢራን ቅዳሜ ዕለት ቱርክን ለቀው ወደ ሜክሲኮ ከሚያመሩት ተጫዋቾቿ ጋር ለሚጓዙት የዓለም ዋንጫ ቡድን የድጋፍ ሰራተኞች ቪዛ በመከልከሏ አሜሪካን ክፉኛ መቸቷን አካቷe።
    9 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም አርብ
    አርስተ ዜና-አሜሪካ በኩባ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ አሳረፈች። --ቅድሚያ ለሰብአዊ መብት የተባለ አገር በቀል የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ እየተካሄደ ነው ባለው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን እንዲያወግዝ እና እንዲያስቆም ጥሪ አቀረበ።--በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቡርጂ እና ጌዴኦ ዞኖች ምርጫ ሲያጭበረብሩ የተገኙ ከስድስት እስከ አሥር ወር እሥራት ተቀጡ ፡፡--የቀድሞ የአዲስ አበባን ከንቲ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።--የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከአራት ዓመታት በላይ የዘለቀው ጦርነት እንዲያበቃ ስምምነት ላይ ለመድረስ ለፑቲን ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ።
    11 min
  • የግንቦት 27 ቀን 2018፤ ዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና ተቃዋሚው የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ ምርጫ«የማጭበርበር ተግባራት ተፈጽሟል» ሲል ቅሬታ ማቅረቡን።የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የተከሰተዉ ሁከት በጥልቅ እንዳሳሰበው ማስታወቁ።በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ችላ ተብለዋል ሲል አንድ የእርዳታ ድርጅት መግለጹን።ሊባኖስ፤ የእስራኤል የድሮን ጥቃቶች መቀጠላቸውን መግለጿ።ኩዌት የኢራን ድሮን አውሮፕላን ማረፊያዋን መምታቱን ማስታወቋን።የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ሀገሪቱ በኢራን የምታደርገውን ወታደራዊ እርምጃ ለማስቆም የቀረበውን ውሳኔ መደገፋቸውን የሚያስቃኙ ዜናዎች የሚሉት ተካተዋል።
    12 min
  • የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን እየሰፋ መጣ ያሉትን ጥቃት የመንግሥት የፀጥታ አካላት ያላቸውን መዋቅር ተጠቅመው እንዲያስቆሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ጠየቁ።
    በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል ሃገራት ኤምባሲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ ያልተካሔደባቸው የምርጫ ክልሎች ድምፅ የመስጠት «ዕድል ይሰጣቸዋል» የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ።
    ዴሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ በኢቦላ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 343 ደረሰ።
    ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ቀጥላለች።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…