የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም አርብ
    አርስተ ዜና -የደቡብ አፍሪቃ ባለስልጣናት ተባብሶ የቀጠለዉን ጥቁር የውጭ ዜጋ ጥላቻን ተከትሎ ጥቃትን በመፍራት ደርባን በሚገኘ አንድ የቤተክርስቲያን ማእከል ዉስጥ ከለላ የጠየቁ አፍሪቃዉያን ከማዕከሉ አስወጡ። ኢትዮጵያዉያንም ይገኙበታል።-ህንድና የአፍሪቃ ህብረት በሚቀጥለው ሳምንት በኒው ደልሂ ሊያካሂዱት የነበረው የመሪዎች ጉባዔ በኮንጎ በተቀሰቀሰዉ የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ። -የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ፈረንሳይ በቅኝ ግዛቶቿ የነበረውን ባርነት ለመቆጣጠር ያገለገሉትን ያረጁ ህግጋቶች እንድታስወግድ እንደሚፈልጉ ተናገሩ። ሕግጋቱ አገራቸዉ ዛሬ ከምትላቸው እሴቶች ጋር አይጣጣሙም ብለዋል።
    13 min
  • የግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ለመንግሥት አቅርቦት የነበረው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በምርጫው ተሳትፎው እጅግ የተቀዛቀዘ እንዲሆን ማድረጉን አስታወቀ ።
    የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ በክልሉ የ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ከታቀደው አንድ ወር ቀደም ብሎ እንደሚያበቃ አስታወቀ።
    ባለፉት 3 ሳምንታት ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ዩጋንዳ ወይም ደቡብ ሱዳን የነበሩ አሜሪካውያን ጠለቅ ላለ ምርመራ ፣በዋሽንግተን ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ብቻ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገቡ የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ ።
    11 min
  • የግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ «አለአግባብ ከምርጫው ተሳትፎ አግልሎኛል» ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መሠረተ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የዕጩዎችን ምዝገባ አጠናቅቄ የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት ጀምሬያለሁ ይላል።
    የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ከጎርጎሪዮሳዊው 2024 ዓ,ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የቆየው የቪዛ ገደብ መነሳቱን አስታወቀ።
    የዓለም የጤና ድርጅት በኤቦላ መሞታቸው የተጠረጠረ ሰዎች ቁጥር 139 መድረሱን ዛሬ አስታወቀ። በተሐዋሲው መያዛቸው የተጠረጠረም 600 ደርሰዋል።
    ሩሲያና ቻይና ለዩክሬን ጦርነት መንስኤ የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች እንዲወገዱ ጥሪ አቀረቡ። በኢራን ላይ የሚደርሰውን ጥቃትም ኮነኑ።
    12 min
  • የማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቐለ፥ «የትግራይ የሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» ምሥረታን ሕወሓት አጣጣለ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዐቃቢያነ-ሕግጋት ከፊል የሥራ ማቆም አደረጉ፤ ኪንሻሳ፥ የኢቦላ ወረርሺኝ አኅጉራዊ የጤና ሥጋት መኾኑ ታወጀ፤ ቤርሊን፥ አሜሪካዊ የኮሮና ታማሚ ጀርመን ለልዩ ኅክምና ተወሰደ፤ ሞስኮ፦ ቤላሩስ ከሩስያ ጋር የኑክሊየር ጦር መሣሪያን የሚያካትት ወታደራዊ ልምምድ መጀመሯን ይፋ አደረገች፤ ካይሮ፥ የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ድልድል ይፋ ኾነ
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
    አርስተ ዜና፦ በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የተባለ ጭማሪ በመደረጉ አገር አቀፍ የትራንስፖርት አድማ ተቀሰቀሰ። ናይሮቢን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ተቃዉሞዉ ቀጥሏል። -ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እንዲሰሩ በድጋሚ የተሾሙት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ያለውን ልዩነት በበለጠ ብልሃትና ስልታዊ አካሄድ መፍታት እንደሚገባቸው ተመለከተ።-የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ቴህራን ላይ ጫና በማሳረፍ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ኢራን ትወድማለች" ሲሉ በድጋሚ ዛቱ።-በፈረንጆቹ 2025 ዓመት በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር የሞት ቅጣት መፈፀሙን፤ አምነስቲ አስታወቀ።
    11 min
  • DW Amharic- የግንቦት 09 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በt,ከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን፣በናይጄሪያ ወታደራዊ ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመ የአክራሪዎች ጥቃት 17 የፖሊስ ሰልጣኞች መገደላቸውን፣በዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የኒኩሌር ማዕከል ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በማዕከሉ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን፣ አሜሪካ ለኢራን የድርድር ሀሳብ በሰጠችው ምላሽ ላይ ምንም አይነት ተጨባጭ የስምምነት ሀሳብ የለውም ሲሉ የኢራን መገናኛ ዘዴዎች መግለፃቸውን እንዲሁም የሰሜን ኮሪያ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት ማድረጉን አካቷል።
    8 min
  • DW Amharic የግንቦት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ኤርትራ እና ግብጽ የባሕር ትራንስፖርት የትብብር ሥምምነት ዛሬ ቅዳሜ በአስመራ ተፈራረሙ። ሥምምነቱ የተፈረመው የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በተገኙበት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢቱሪ ግዛት በኢቦላ ወረርሽኝ ቢያንስ 80 ሰዎች ሞቱ። የቦኮ ሐራም አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከፈጸሙት ጥቃት በኋላ ቢያንስ 42 ልጆች ደብዛቸው መጥፋቱን የአካባቢው ተመራጭ ተናገሩ። የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ኢዚዲን አል-ሐዳድ ተገደሉ።
    9 min
  • የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    -በደቡብ አፍሪካ የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ጋብ አያለ ቢመጣም «ሕገ ወጥ ግንባታ» በሚል ምክንያት ሱቆቻቸው እየፈረሱባቸው እንደሚገኙ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያዊያውያን ለዶቼቬለ ተናገሩ ።
    -በኮንጎዋ ኢቱሪ ክፍለ ሀገር በተከሰተ አዲስ የኤቦላ ወረርሽኝ 65 ሰዎች መሞታቸውን መታወቁን የአፍሪቃ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል አስታወቀ።
    -የብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሁለት ቀናት ኒው ዴልሂ ህንድ ውስጥ ያካሄዱትን ጉባኤ የጋራ መግለጫ ሳያወጡ ዛሬ አበቁ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 6 ቀን 2018 ሐሙስ
    አርስተ ዜና -የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና በፕሬዚዳንት ዢ ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸዉ። ትራምፕ አስደናቂ መሪ ሲሉ ዢ ጂንፒንግን አሞካሽተዋቸዋል። የሁለቱ ሀገራት "የተረጋጋ" ግንኙነት ለዓለም ፋይዳ እንደሚሆን የተናገሩት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸዉ፤ የታይዋን ጉዳይ በአግባቡ ካልተያዘ ግን ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።-ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ በዩናይትድ ስቴትስ ከ4 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ መነሳቱ ተገለፀ። ዩናይትድ ስቴትስ ኤርትራ ላይ የጣለችዉን ማእቀብ ለማንሳት እያሰበች እንደሆን ያስታወቀችዉ በዚሁ ሰሞን እንደሆን የሚታወስ ነዉ።
    15 min
  • የግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ትናንት ከአሶሳ ወደ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ይጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የበርካቶች ሕይወት አለፈ።
    የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማኑዌል ማክሮ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፈረንሳዩ መሪ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው አመልክተዋል።
    ጋና ከደቡብ አፍሪቃ 300 ዜጎቿን ልታወጣ መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
    የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ከቀትር በኋላ ቻይና ገብተዋል። የትራምፕ ጉዞ በ9 ዓመት በአሜሪካ ፕሬዝደንት ወደ ቻይና የተደረገ የመጀመሪያ ጉብኝት ነው።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…