የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የግንቦት 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -አርዕስተ ዜና
    -በጅቡቲ ወይም በሶማሊያ በኩል የአደን ባሕረ-ሠላጤን አቋርጠዉ ወደ አረብ ሐገራት ለመሰደድ የሚሞክሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ቢሞቱም፣ ሌሎች መሰደዳቸዉን አለማቆማቸዉን ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ድርጅት አስታወቀ።-የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ የሚደረጉ ግጭቶችን ለማስወገድ ኢትዮጵያ «ጠቃሚ» ያሉትን ሚና እየተወጣች ነዉ በማለት አደነቁ።--ፈረንሳይ ከአፍሪቃ ሐገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት በአ,ዲስ መልክ እንደምታጠናክር አስታወቀች።ፈረንሳይ ከቀድሞ ቅኝ ግዛቶችዋ ከፈረንሳይኛ ተናጋሪ የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ጋር ከተቃቃረች ወዲሕ ፊቷን ወደ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎቹ አዙራለች
    11 min
  • የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ፣የክስ ሂደታቸው "በኘላዝማ" እንዲታይ ተወስኖባቸው የነበሩ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ሥር ያሉ የሽብር ተከሳሾች ጉዳያቸውን በአካል እንዲከታተሉ ዛሬ ብይን ሰጠ።
    ሱዳን ውስጥ በተፈጸሙ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮኖች) ጥቃቶች ከጥር እስከ ሚያዚያ ቢያንስ 880 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የተመድ አስታወቀ።
    በተመድ የአፍሪቃ ውክልና እንዲጨምር የተሀድሶ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ አሳሰቡ ።
    13 min
  • የግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በሰሜናዊ ምስራቋ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት ኢቱሪ 69 ሰዎች በሚሊሺያዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች እና የጸጥታ አካላት ተናገሩ።
    • በማዕከላዊ ማሊ በተመሳሳይ ጂሃዲስቶች አደረሱ በተባለ መጠነ, ሰፊ ጥቃት በ,ርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የጸጥታ ምንጮች ትናንት ቅዳሜ አስታወቁ።
    • ኢራን አሜሪካ ላቀረበችላት የሰላም ስምምነት መልስ መስጠቷን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ዘገቡ ።
    • ሩስያ በዩክሬን የምታደርገው ጦርነት በፍጥነት እንዲያበቃ ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች።
    • በሃንታ ቫይረስ በተመታች የመዝናኛ መርከብ ላይ ያሉ ተጓዦችን የማስወጣት ስራ በይፋ ተጀመረ።
    9 min
  • የቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አከባቢ ባለፈው ሓሙስ «በአንድ የፖሊስ አባል የተገደለ» ወጣት ትናንት ዓርብ ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙን ፤የናይጄሪያ ጦር በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል 50 ፅንፈኛ ያላቸውን ታጣቂዎች መግደሉን ማስታወቁን፤የዓለም ጤና ድርጅት ሀላፊ የሃንታ ቫይረስ የተከሰተበት መርከብ ከመድረሱ በፊት ስፔን መግባታቸው መገለፁን፤ ሂዝቦላህ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት ማድረጉን መግለፁ፣ሞስኮ በጠንካራ ጥበቃ ስር ዛሬ የድል ቀን በዓልን ማክበሯን፣ኢራን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ማስታወቋን አካቷል።
    12 min
  • የዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቐለ፥ሕወሓት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ ዛሬበይፋ ሥራ መጀመሩን ዐሳወቀ፤ ናይሮቢ፥ የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ሦስት የአፍሪቃ አገራትን ሊጎበኙ ነው፤ ሞቃዲሾ፥ ሶማሊያ ውስጥ ብርቱ የረሐብ አደጋ እልቂት እንዳይፈጥር አስግቷል፤ ሪያድ፥ በኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ ዘመቻዋ ዩናይትድ ስቴትስ የዓየር ክልሏን እንዳትጠቀም ሣዑዲ ዓረቢያ አገደች፤ ቴህራን፥ ኢራን መርከቦቼ ላይ ጥቃት አደረሰችብን ያለቻት ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቀች፤ ዋሽንግተን፥ ዩናይትድ ስቴትስ የኢራን መርከቦች ላይ ተኩስ ከፈተች
    11 min
  • የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    -ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉ ይበልጥ እንዳሰጋቸው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ ተናገሩ።
    -የናፍጣ እጥረት ባናረው የጭነት መጓጋዣ ዋጋ ምክንያት፣ የሙዝ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቸገራቸውንና ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑንም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ሙዝ አምራች አርሶ አደሮች ዐሳወቁ።
    -ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ የኢራኑን ጦርነት ለማስቆም ያቀረበችውን የሰላም እቅድ እየገመገመች መሆኑን ኢራን አሳወቀች።
    11 min
  • ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን ጥቃት) እጄ የለበትም ስትል አስተባበለች ።
    • የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በቻድ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 23 ወታደሮች ተገደሉ ፤ ሌሎች 26 ቆሰሉ ።
    • አሜሪካ እና ኢራን የባሕረ ሰላጤውን ጦርነት ለማቆም ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸው ተሰማ።
    • በገዳዩ የሀንታ ተሐዋሲ የተጠረጠሩ ሦስት ተጓዦች ከመንገደኞች መርከብ ተለይተው ወደ ኔዘርላንድስ መወሰዳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
    10 min
  • የማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቀለ፥ ሕወሓት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልን የትግራይ ክልል ፕረዚደንት አድርጎ መረጠ፤ ናይሮቢ፥ ኢትዮጵያና ሱዳን አንዱ ሌላኛውን በማጥቃት እየተካሰሱ ነው፤ አስመራ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ልታነሳ ነው መባሉ፤ ዋሽንግተን፥ ዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ ሠርጥ መርከቦችን ብታስተናብርም የተኩስ አቁሙ ግን እንደተጠበቀ ነው አለች፤ ዬርቬና፥ የአውሮጳ ኅብረት የትራምፕ የቀረጥ ዛቻ ለሚያስከትለው ማንኛውም ነገር ዝግጁ መሆኑን ዐሳወቀ፤ ለንደን፥ ዩክሬንን ለማጥቃት ለሩስያ ተዋጊዎችን የሚመለምሉ ላይ ብሪታንያ ማእቀብ ጣለች፤ ላይፕትሲሽ፥ በተሽከርካሪ ግድያ የፈጸመው ግለሰብ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
    አርስተ ዜና--የጀርመን መራሄ መንግሥት ፍሬድሪክ መርስ ፤ ዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 5,000 የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን ጦር ሰፈር ለማዉጣት ማቀዳቸዉ የሚያስደንቅ እንዳልሆነ ተናገሩ። ኔቶ በበኩሉ አውሮጳውያን፤ የአሜሪካኑን ፕሬዝዳንት የብስጭት መልእክትን «ሰምተው» ቁርጠኝነታቸዉን እያጠናከሩ ነዉ ሲል መልስ ሰጥቷል።-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ኢሶዴፓ) ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያቀረባቸውን 309 ዕጩዎች ከውድድሩ ውጪ ማድረጉን አስታወቀ። -በእስር ላይ የሚገኙ ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ጋር ቅርበት ያላቸው ሰባት ሰዎች መካከል እስካሁን ፍርድ ቤት በቀረቡት ሁለቱ ላይ ፖሊስ የ14 ቀን ቀጠሮ ጠይቋል።
    12 min
  • የሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በመዲናዪቱ ካርቱም (RSF) ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት አምስት ንጹሐን ዜጎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች አስታወቁ።
    • በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ሌላ የነዳጅ መርከብ በባሕር ላይ ወንበዴዎች ተጠለፈች
    • ኢራን በ30 ቀናት ውስጥ ግጭቱ እንዲቆምና የአሜሪካ ማዕቀቦች እንዲነሱ የሚጠይቅ የ14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ አቀረበች።
    • ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሃኑ ወንድሙ ዛሬ የተካሄደውን 31ኛው የፕራግ ዓለም አቀፍ ማራቶን አሸነፈ።
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…