ጠ/ሚ አብይ አህመድ በቀይ ባሕር ወደብ ምክንያት መንግሥታቸው ከኤርትራ ጋር ወደግጭት አይገባም አሉ። የባሕር በር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው ያሉት አቢይ ይህ ግን በሰላማዊ ንግግርና በሰጥቶ መቀበል እንደሚሆን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ በሁሉም ሠራተኞች ላይ አዲስ የግብር ዓይነት ይፋ አደረገ። አዲሱ የግብር ዓይነት በመንግሥትም ሆነ በግል ዘርፎች ተቀጥረው በሚሠሩ ላይ ተግባራዊ የሚሆን ነው።
በሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱምና በአካባቢው በርካታ ሲቪሎች በቦምብና በሞርታር እየተገደሉ ነው ሲል የተመድ ዛሬ አስታወቀ።
የአውሮጳ ሕብረት መሪዎች የአውሮጳን የጦር አቅርም ለማጠናከር ብራስልስ ላይ ተሰባስበው እየመከሩ ነው።