የአርብ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓም ዐርዕስተ ዜና
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን የዩኒቨርሲቲ መምህራንና የሕግ ጠበቆችን ጨምሮ ሰዎች በጅምላ እየታፈሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች እና የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼቬለ ተናገሩ። የከተማይቱ ነዋሪዎች እንደሚሉት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አንዳንዶች ከመኖሪያ ቤታቸው ሌሎች ደግሞ ከመንገድ ላይ እየተያዙ ነው።
የሱዳን ጦር፣ የመንግስት መቀመጫ የሆነውን የካርቱምን ቤተ መንግሥት መልሶ መቆጣጠሩን ዛሬ አስታወቀ።
የጀርመን ላዕላይ ምክር ቤት ቡንደስራት ፣በሀገሪቱ የብድር ሕግ ገደብ ላይ ታሪካዊ ማሻሻያ አደረገ።