የመጋቢት 17 ቀን 2017 ዓም ዐርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትግራይ ሕዝብ ለሚቀጥለው አንድ አመት የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳድር ፕሬዝዳንት ሊሆን የሚችል ሰው እንዲጠቁም ጥሪ አቀረቡ።
የጀርመን ፖሊስ ፣ የኤርትራን መንግስት የመገልበጥ ዓላማ አለው የተባለውን እና የዓለም አቀፍ መረብ አካል መሆኑ የተገለጸ ብርጌድ ንህመዱ የተባለው ቡድን የጀርመን ቅርንጫ ላይ ፣ዛሬ በስድስት የጀርመን ፌደራዊ ግዛቶች ልዩ ፍተሻ ማድረጉን አስታወቀ።
የሱዳን ጦር ፤ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ተቆጣጥሮት የነበረውን የኻርቱምን አውሮፕላን ማረፊያ መልሶ መያዙን አስታወቀ።