-ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ በአዉቶቡስ ሲጓዙ ኦሮሚያ ክልል ካንድ ሳምንት በፊት የታገቱት መንገደኞች ያሉበት ሥፍራና ሁኔታ እስካሁን አለመታወቁ ተነገረ።መንገደኞቹ ሲታገቱ ያዩ እንደሚሉት የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች በአጋቾቹ ላይ ተኩስ ቢከፍቱም ታጋቾቹን ማስጣል ግን አልቻሉም።-አዲስ አበባ ዉስጥ በልማዱ ሰባራ ባቡር በተባለዉ አካባቢ ዛሬ ጠዋት የተነሳ የእሳት ቃጠሎ ሁለት የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞችን አቆሰለ።ሶስት መደብሮችንም አጋየ።-በሩዋንዳ የሚደገፈዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አማፂ ቡድንና የሐገሪቱ መንግስት ጦር የገጠሙት ዉጊያ መዘዝ ለአካባቢዉ ሐገራት ሊተርፍ እንደሚችል የኬንያ ፕሬዝደንት አስታወቁ።