የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና ፤ የትንሳኤ በዓል በኦርቶዶክስ ክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ በመላው ዓለም መከበሩን ፣በቤኒኒናውያን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ መዋላቸውን፣አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን ባደረጉት ውይይት ስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸውን፣ኩዌት በሐገር ደሕንነት ላይ ያነጣጠረ የሽብር ሴራን አከሸፍኩ ማለቷን እና ሳውዲ አረቢያ በድሮንና በሚሳይል ጥቃቶች ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የሓይል መሰረተ ልማቶችን ጠግና ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጓን ያስቃኛል።
    8 min
  • የሚያዝያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያ ውስጥ የከርቤ ዛፍ በድርቅ ምክንያት እየተመናመነ እንደሆነ አሶሺየትድ ፕረስ ዘገበ። የጅቡቲው ፕሬዝደንት ጉሌሕ 97.81% የመራጭ ድምፅ በማግኘት አሸነፉ።
    የእስራኤል ጦር ባለፉት 24 ሰዓታት ሊባኖስ ውስጥ ከ200 በላይ የሂዝቦላ ኢላማዎች መደብደቡን አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊዎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚደረግ የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት እንዲቆም ጠይቁ። የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ የፊት ለፊት ድርድር ዛሬ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ጀምሯል።
    ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ አቅራቢያ የነበሩት የጠፈር ተመራማሪዎች በሰላም ወደ ምድር ተመለሱ።
    11 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በዎላይታ ዞን ከባድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ 7 ሰዎች ሲሞቱ 6 ተጎዱ። ኢሕአፓ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ቅንጅትን ወክለው ለድሬደዋ ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ አባሉን እስር አወገዘ። የጅቡቲ ዜጎች ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ያሸንፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ጄድ ቫንስ በኢዝላማባድ ድርድር ኢራን ዩናይትድ ስቴትስን "ለማታለል" እንዳትሞክር አስጠነቀቁ። የኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ ድርድሩ ከመጀመሩ በፊት በሊባኖስ የተኩስ አቁም መደረግ እንዳለበት ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል።
    12 min
  • የሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ባገረሸው የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ተሰማ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በመጪዉ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በ10 የኢትዮጵያ ከተሞች የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያከናውን አስታወቀ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶንዮ ጉተረዥ ኢራን በሊባኖስ ስቪል ዜጎችና መሰረተ ልማቶች ላይ የፈጸመችውን ጥቃት በጥብቅ አወገዙ።
    11 min
  • የመጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ቀዬያቸው ተፈናቀሉ።
    የጅቡቲ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ዓርብ የሚካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚያሸንፉ እየተጠበቀ ነው።
    እስራኤል በኢራን የሚደገፈውን የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ለማጥቃት በሚል ሊባኖስን ደብድባለች።
    የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩተ ዛሬ በዋይት ሀውስ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
    በኢራን እና በአዘርባጃን የባህር ዳርቻዎች ዛሬ በሬክተር ስኬል መለኪያ 5.6 የነበረ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።
    11 min
  • የመጋቢት 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ከ80 የሚበልጡ ስደተኞች ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ ሰምጠዉ ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) እንደሚለለዉ 120 ስደተኞች አሳፍራ ከሊቢያ ወደ አዉሮጳ ትቀዝፍ የነበረች አነስተኛ ጀልባ ባለፈዉ ዕሁድ ሰጥማለች።32ቱ በሕይወት ተርፈዋል።-----የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦር ኃይላት አንዳቸዉ የሌላዉን ተቋማትና ይዞታዎች በደብደባቸዉን ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ።የቃላት ጦርነቱም እንደናረ ነዉ።---ጦርነቱ የእርዳታ ምግብ፣መድሐኒትና ቁሳቁስ እንዳይንቀሳቀስ ወይም እንዲዘገይ ማድረጉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች አስታወቁ።
    13 min
  • የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    እሥራኤልና አሜሪካ ዛሬ በኢራን ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ25 ሰዎች በላይ ተገደሉ። ከመካከላቸው የኢራን ፈጥኖ ደራሽ አብዮታዊ ዘብ የስለላ ክፍል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ማጃድ ክሀዴሚ ይገኙበታል። በሌላ በኩል ዛሬ በእሥራኤል ላይ ዛሬ ከኢራን ከሂዝቦላ እና ከየመን በተመሳሳይ ጊዜ ጥቃቶች ተፈጽመውባታል
    ኢራንና ዩናይትድ ስቴትስ ለ45 ቀናት የተኩስ አቁም እንዲያደርጉና የሆርሙዝ ሰርጥም እንዲከፈት የቀረበውን ረቂቅ ምክረ ሃሳብ ኢራን እንደማትቀበለው አስታወቀች
    የናይጀሪያ ጦር ት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተፈፀሙ ሦስት ጥቃቶች ቢያንስ 26 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቁ ።
    13 min
  • የመጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ከሊብያ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ ለማሻገር ትቀዝፍ የነበረች ጀልባ በሜዲትራንያን ባሕር በመስጠሟ ከ70 በላይ ስደተኞች እስከ አሁን ደብዛቸው አልተገኘም። ሰሜንናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ ታጣቂዎች ትናንት ቅዳሜ በፈጸሙት ጥቃት አራት የፖሊስ መኮንኖች ተገደሉ ። ኢራን በዛሬው ዕለት በኬዌትና በባህሬን የሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ብርቱ ጥቃት መፈጸሟን የየሐገራቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
    7 min
  • የመጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና፤ የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ከአንድ ሺ ለሚበልጡ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ፤ሴኔጋል ከኢራን ጦርነት ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የነዳጅ ወጭ ለመቀነስ የባለስልጣናትን የውጭ ጉዞ መገደቧን፣ የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቶች ኢራን ውስጥ ዛሬም በርካታ ቦታዎችን ኢላማ ማድረጋቸውን፣ የተባበሩት መንግስታት የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን ለማስከፈትን በተመለከተ ለዛሬ ታቅዶ የነበረው ድምጽ አሰጣጥ ለሌላ ጊዜ መገፋቱን ፤አሜሪካ በኢራን ተመቶ ከወደቀ አውሮፕላን አንድ አብራሪዋን መታደጓን ባለስልጣናት መግለፃቸውን እና ኔዘርላንድ በሚገኝ አንድ የእስራኤል ደጋፊ ማዕከል ላይ ፍንዳታ በመከሰቱን ያስቃኛል።
    12 min
  • የመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና፤ በሀዋሳ ከተማ በመኪና አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በአንድ ሆስፒታል ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን፤የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት አሜሪካ በሀገራቸው ላይ የጣለችው ማዕቀብ «ለሩዋንዳ ስድብ» ሲሉ መግለፃቸውን፤በኢራን ጦርነት የነዳጅ ዋጋ በማሻቀቡ የምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ማስታወቁን፤ኢራን እና እሥራኤል አንዳቸው በአንዳቸው ላይ የሚፈፅሙትን ጥቃት መቀጠሉን፤ ኢራን ዉስጥ አንድ የአሜሪካተዋጊ ጄት ተመትቶ ወደቀ መባሉን እንዲሁም ፈረንሳይ እና ደቡብ ኮሪያ የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት በጋራ እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ያስቃኛል።
    14 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…