የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኬኒያ ሲሻገሩ ደረስኩባቸው ያላቸውን 48 ኤርትራዊያንን በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ አስታወቀ ፡፡
    • የናይጄሪያው ግዙፉ የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ነዳጅ መላክ መጀመሩን አስታወቀ።
    • ማሊ በነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎቿ ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማስቆም በደረሰችው ስምምነት በርካታ ጂሃዲስቶችን ከእስር ለቀቀች።
    • የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወሳኙን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ለአለም አቀፍ የንግድ መርከቦች እንድትከፍት ያስቀመጡትን የጊዜ ገደብ ለአምስት ቀናት ማራዘማቸውን አስታወቁ።
    12 min
  • የመጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ 13 ሕፃናትን ጨምሮ በትንሹ 64 ሰዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
    • ኢራን በእስራኤል የበረሃ ከተሞች ላይ በፈጸመችው የሚሳኤል ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች ቆሰሉ ።
    • በቃጣር በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን የቃጣር እና የቱርክ ባለስልጣናት አስታወቁ። • ቱርክ፣ እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ሰላማዊ ዕልባት እንዲያገኝ ጥረት እያደረገች መሆኑ ተሰማ።
    10 min
  • የመጋቢት 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እና የኬንያ መዲና ናይሮቢን ጨምሮ በአስራ ሁለት ከተሞች የአደጋ እና ሰብአዊ ድጋፍ ምላሽ ቀጠናዊ ማዕከላት ልታቋቁም ነው። ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል በኢራን ኢስፋሃን ግዛት የሚገኘው የናታንዝ የኒኩሊየር ማብለያ ጣቢያ ላይ በድጋሚ ጥቃት መፈጸማቸውን የኢራን መገናኛ ብዙሃን አስታወቁ። እስራኤል በሶሪያ ጦር ካምፕ የፈጸመችው ጥቃት ሳውዲ አረቢያ «ወረራ» ስትል አወገዘችው።
    11 min
  • የመጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    1447 ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፊጥር በዓል ዛሬ አዲስ አበን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ በእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሯል። የእስራኤል ጦር ዛሬ ጠዋት በቴህራን ባካሄደው ድብደባ የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ ቃል አቀባይ መግደሉን አስታወቀ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ታላቋ ብሪታንያን አስጠነቀቁ። የፈረንሳይ የባሕር ሐይል አባላት የሩስያ ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን የሐገሪቱ ፕረዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤክስ ገጻቸው ገልጸዋል።
    10 min
  • የሐሙስ መጋቢት 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አአ፥በሰው ሠራሽ አስተውሎት ወይም 'AI' የተሠሩ ምስሎች ሚና በኢትዮ ኤርትራ ወታደራዊ ውጥረት፤ አ.አ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ወቅታዊው የነዳጅ እትረት ማጓጓዣ ስርዓቱ ላይ ተግዳሮት ፈጥሯል፤ ንጃሜና፥ ከሱዳን የተሰነዘረ የሰው አልባ ጥቃት ጎረቤት ቻድ ውስጥ 17 ሰው ገደለ፤ ላሙ፥ በኢራን ጦርነት የተነሳ በሺህዎች የሚቆጠሩ ፖርሼ ተሽከርካሪዎች ኬኒያ ተራገፉ፤ ብራስልስ፥ በአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ላይ የተገኙት የተመድ ዋና ጸሐፊ የኢራን ጦርነት እንዲያበቃ ጥሪ አስተላለፉ፤ ቴሕራን፥ ኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ ላይ መርከቦችን ለማስከፈል እያጤንኩ ነው አለች
    13 min
  • የመጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው በዋስ እንዲለቀቁ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ ዛሬ ውድቅ አደረገው። የተከ
    የእስራኤል ጦር ኃይል የኢራንን የስለላ ጉዳይ ሚንስትር ኢስማኢል ኻቲብን መግደሉን አስታወቀ። ኢራን ግድያዉን አላረጋገጠችም።
    የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና እሥራኤል በኢራን ላይ ስለከፈቱት ጦርነት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለጀርመን አማክራ ቢሆን ኖሮ፣ እርምጃው እንዳይወሰድ እንመክራቸው ነበር ሲሉ አስታወቁ። ሜርስ እንዳሉት ዋሽንግተን ስለጦርነቱ ጀርመንን አላማከረችም።
    11 min
  • የመጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የደቡብ ሱዳን ጦር እና በአማጽያን መካከል የተቀሰቀሰውን አዲስ ግጭት ሽሽት ከ100 ሺ በላይ የአኮቦ ከተማ ነዋሪዎች ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አስታወቀ። • የሶማሊያዋ የጁባላንድ ግዛት አስተዳደር ከሞቃዲሾው ፌዴራላዊ መንግስት ጋር ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት እና ትብብር ማቋረጡን አስታወቀ። • በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ በደረሰ ተከታታይ የአጥፍቶ መጥፋት የቦምብ ጥቃት በትንሹ 23 ሰዎች ተገደሉ። • እስራኤል ከፍተኛውን የኢራን የደህንነት ባለስልጣን አሊ ላሪጃኒን መግደሏን አስታወቀች።
    12 min
  • የመጋቢት 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በኢትዮጵያ “ነዳጅን በቁጠባ እና ለመሰረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም” እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ።የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀዘናቸውን ለኢትዮጵያ ገለፁ። ኬንያ ፤ ሩሲያ የኬንያ ዜጎችን ለውትድርና መመልመሏን ለማቆም ተስማማች። ኢራን በኳታር እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ ጥቃት ሰነዘረች። ትራምፕ „የኔቶ አባል ሀገራት አሜሪካን ካላገዙ የኔቶ የወደፊት እጣ ፈንታ ጥሩ አይሆንም” አሉ።
    11 min
  • የመጋቢት 06 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ ላይ ያደረገውን ጭማሪ ተከትሎ በአዲስ አበባ የሕዝብ መጓጓዣ ከ5 እስከ 20 ብር የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ። የሩሲያ ጦር በዩክሬን በመካሔድ ላይ ለሚገኘው ጦርነት ኬንያውያንን በግዳጅ ከመመልመል እንዲታቀብ ግፊት ለማድረግ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ወደ ሞስኮ አቀኑ። በኮንጎ ሪፐብሊክ ዜጎች ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን የገጠሙትን ጦርነት የቀሰቀሱ መሪዎች ውጊያውን እንዲያስቆሙ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ሊዎ 14ኛ ጥሪ አቀረቡ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በባርሴሎና እና በሴዑል የተካሔዱ የማራቶን የሩጫ ውድድሮችን አሸነፉ።
    11 min
  • የመጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በታንዛኒያ ኃይቅ ላይ ጀልባቸው ተገልብጦ ሰባት የጤና ባለሙያዎች ህይወት አለፈ።የዩጋንዳ ተቃዋሚ መሪ ቦቢ ዋይን ከሀገር መውጣታቸውን አስታወቁ።አሸዋ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ በእስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ እየነፈሰ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ኻመኔይና ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለመያዝ 10 ሚሊዮን ወሮታ እከፍላለሁ አለች። በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳት ደረሰበት።ሰሜን ኮሪያ አስር የሚጠጉ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…