የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በታንዛኒያ ኃይቅ ላይ ጀልባቸው ተገልብጦ ሰባት የጤና ባለሙያዎች ህይወት አለፈ።የዩጋንዳ ተቃዋሚ መሪ ቦቢ ዋይን ከሀገር መውጣታቸውን አስታወቁ።አሸዋ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ በእስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ እየነፈሰ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ኻመኔይና ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለመያዝ 10 ሚሊዮን ወሮታ እከፍላለሁ አለች። በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳት ደረሰበት።ሰሜን ኮሪያ አስር የሚጠጉ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች
    12 min
  • የዓርብ መጋቢት 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ጋሞ፥ በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ለ3 ቀናት የሚቆይ ክልላዊ የሐዘን ቀን ታወጀ፤ አስመራ፥ ኤርትራ ውስጥ ያለ ክስ ለ15 ዓመታት የታሰረ ካርቱኒስት መፈታቱ ተገለጠ ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በጊዜያዊነት የሩስያ ድፍድፍ ነዳጅ እገዳን አነሳች፤ ኪዬቭ፥ የሩስያ ነዳጅ እገዳ በከፊል መነሳት ተቃውሞና ድጋፍ፤ ካቡል፥ ፓኪስታን የአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና የድንበር ከተሞችን በቦንብ ደበደበች፤ ዋሽንግተን፥ የታይዋን ምክር ቤት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነትን አጸደቀ፤
    11 min
  • የመጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ዐርእስተ ዜና
    አሜሪካን የጠረዘቻቸው 4 ተጨማሪ ሰዎች ኤስዋቲኒ ተቀበለች ተጠራዦች ሁለቱ ከሶማሊያ አንድ ከታንዛኒያ ሌላ አንድ ደግሞ ከሱዳን መሆናቸው ተገልጿል።
    አዲሱ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ኻማኒ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጡት መግለጫ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መዘጋት እንደ ማነቃቂያ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ተናገሩ፤ ኢራን ጎረቤቶቿን የባህረ ሰላጤው አገራትን ማጥቃቷን እንደምትቀጥልም አስታወቁ
    ቱርክና ጀርመን የኢራን ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ተስማሙ። ጀርመን አውሮጳውያንና የባህረ ሰላጤው አገራት የኢራንን ጦርነት ለማስቆም በጋራ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ ጥሪ አቀረበች።
    12 min
  • የመጋቢት 2 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ደቡብ ኢትዮጵያ ጋሞ ዞን ዉስጥ በደረሰ የመሬት መደርመስና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 64 ሰዎች ሞቱ።ሌሎች በርካታ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።---ሱዳን ዉስጥ ለቀስተኞችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አነስተኛ የጭነት መኪና (ፒክ አፕ) በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) ተመትታ 40 ሰዎች ተገደሉ።በሌላ የሰ,ዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃት 17 ሰዎች ተገድለዋል።አብዛኞቹ ሴት ተማሪዎች ናቸዉ።---እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራን አፀፋ የዓለምን ምጣኔ ሐብት እያዉገረገረዉ ነዉ።ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ መንግስታትና የኃይማኖት መሪዎች የሚያደርጉት ጥሪና ፀሎት እንደቀጠለ ነዉ።ጦርነቱም አላባራም።
    11 min
  • የዓለም ዜና ፤ መጋቢት 1 ቀን 2018 ማክሰኞ
    አርስተ ዜና፤-የኢራን ሲቪሎች ከአሜሪካና ከእስራኤል የአየር ጥቃቶችና በኢንተርኔት መቆራረጥ ያለምንም ከለላ አጣብቂኝ ዉስጥ ናቸዉ። የአገዛዙ ተቃዋሚዎችም ጦርነቱ በቅርቡ ያበቃል የሚል ተስፋ እያጡ ነው። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ጦርነቱ በቅርቡ ያበቃል ማለታቸዉን ተከትሎ የዓለም የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።-ዩናይትድ ስቴትስ ፣የሱዳኑን የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበርን አሸባሪ ድርጅት ብላ ለመፈረጅ መወሰኗን የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አወደሰች።-የአውሮጳ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን፤ አውሮጳ ከኒውክሌር ኃይል ምንጭ ጥቅም ማፈግፈጓ "ስልታዊ ስህተት" ነበር፤ ሲሉ ተናገሩ።
    13 min
  • የየካቲት 30 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና
    የደቡብ ሱዳን ጦር የተቃዋሚ ኃይሎች በሚገኙባት አኮቦ ግዛት ወታደራዊ ዘመቻ ለመክፈት ዜጎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ በማዘዙ በሺህዎች የሚቆጠሩት ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸው ተሰማ።
    በናይሮቢ ኬንያና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 42 መድረሱን መንግሥት አስታወቀ።
    ከእስራኤል እና አሜሪካን ጋር በሚሳኤልና በሰው አልባ አውሮፕላኖች እየተፋለመች የምትገኘው ኢራን አቋሜን አልለወጥኩም አለች። የሟቹን ሃይማኖታዊ መሪ አሊ ኻሚኒን ልጅም በእግራቸው ለመሪነት መርጣለች።
    እስራኤል በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የሊባኖስ ግዛቶች የተጠናከረ ጥቃት ቀጥላለች። ሂዝኮላኽም በጥቃቱ መግፋቱን አስታውቋል።
    10 min
  • DW Amharic የየካቲት 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን አሰናብቶ አዲስ መሪ መምረጡን አስታወቀ። የቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሕመት ማኪ ሳል ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊነት በእጩነት መቅረባቸውን ደገፉ። የኢራን አዲስ መሪ የሚረጠው በሀገሪቱ ሕዝብ እንጂ በዶናልድ ትራምፕ እንደማይሆን የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ተናገሩ። እስራኤል በሊባኖስ ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ባለፈው ሣምንት ብቻ 394 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። ሩሲያ የዩክሬን የጋዝ ማምረቻዎችን ለሁለት ቀናት መደብደቧን የሀገሪቱ የኢነርጂ መሥሪያ ቤት አስታወቀ።
    11 min
  • የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተዋጊዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል በሚል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያቀረበበትን ክስ አጣጣለ፡፡
    • በኬንያ መዲና ናይሮቢ በተከሰተ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ በትንሹ የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
    • የደቡብ ሱዳን ጦር የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይልና ሌሎች ድርጅቶች በአማጽያን ይዞታ ስር ካሉ አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ አሳሰበ።
    • የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በደቡባዊ እና ምሥራቃዊ ሊባኖስ በሚገኙ የሂዝቦላህ የጦር ሰፈሮች ላይ ከፍተኛ የአየር ድብደባ ማድረጉን ዛሬ ቅዳሜ አስታወቀ።
    14 min
  • የየካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የኦሮሞ ነፃነት ጦር አባላት በአዳጊና አዋቂ ሴቶች ላይ የፈጸሟቸውን አስገድዶ መድፈር፣ የቡድን ወሲባዊ ጥቃት፣ የወሲብ ባርነት፣ አሰቃቂ ግድያና ጾታዊ ጥቃቶችን መርምረው አጥፊዎች እንዲጠየቁ እንዲደርጉ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ።
    የተመድ ዩጋንዳ ሲቪሎች የተገደሉበትና ክፉኛ የተቃጠሉበትን የደቡብ ሱዳንን የአየር ጥቃት አግዛለች የሚል መረጃ ይፋ አደረገ።
    በመካከለኛው ምሥራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት ሰባተኛ ቀን የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ቴህራንና ቤይሩትን መደበብደባቸው እየተዘገበ ነው።
    በፓኪስታንና አፍጋኒስታን ግጭት 56 ሲቪል የአፍጋን ዜጎች መገደላቸውን ከመቶ በላይም መጎዳታቸው የተመድ አስታወቀ።
    14 min
  • የየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የህወሓት ምክትል ሊ/መንበር የፌደራል መንግሥት በትግራይ ላይ ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ሲሉ ተናገሩ። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግን በትግራይ ጦርነት እንደማይከፈት አረጋግጣለሁ ብለዋል። ይሁንና ህወሓት ወታደራዊ ትንኮሳ ከገባ ግን«እንደ ቀድሞ መስሎሽ ጎርፍ ይወስድሻል» ብቻ ነው ማለት የሚቻለው» ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
    ከስድስት ወረዳዎች ተፈናለው በቆቦና ሰቆጣ ከተማ የሚገኙት ቁጥራቸው 100 ሺህ ይደርሳል የተባለ ሰዎች ለአንድ ወር የምግብ ድጋፍ እንዳላገኙ ተናገሩ።
    አል ሞጅላድ በተባለ የሱዳን ከተማ ዛሬ የተፈጸመ የድሮን ጥቃት 18 ሰዎችን ገደለ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…