የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የካቲት 25፣ 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ ዳግም ባገረሸ የታጣቂዎች ጥቃት ሶስት የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ 7 ሰዎች ተገደሉ።
    • በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በታጣቂዎች እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎች እና ግፎችን ለማስቆም የኦሮሚያ ክልል እና የፌዴራል መንግስቱ ተጨባጭ ርምጃዎችን እንዲወስድ ኢሰመኮ አሳሰበ ።
    • ደቡባዊ ጂቡቲ ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ አራት ህጻናት መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ግን ህጻናቱ በድሮን ጥቃት መገደላቸውን ገልጿል።
    • ኢራን ከባህረ ሰላጤው ሃገራት በተጨማሪ የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ሃገራት የተሻገረ የሚሳኤል ጥቃት መሰንዘሯ ተሰማ።
    11 min
  • የማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ የተነሳ የድሮን ጥቃቶች ተፈጽሞብኛል ሲል መክሰሱ፤አራተኛ ቀኑን በያዘው ግጭት በቴህራን አዳዲስስ ጥቃቶች መቀጠላቸውን፣ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በሊባኖስ ቢያንስ 30,000 ሰዎች ተፈናቅለዋል መባሉን፣ፑቲን በነዳጅ መሠረተ ልማት ላይ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች የአረብ ስጋቶችን ለኢራን እንደሚያደርሱ መገለፁ ፤የጀርመን ፖሊስ በኢራን ጦርነት የተስተጓጎሉ ተጓዦች በረራዎችን እንደገና ማስያዝ እንችላለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማስጠንቀቁ እናበሰሞኑ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት 30,000 የሚደርሱ የጀርመን መንገደኞች በመካከለኛው ምስራቅ እየተጉላሉ መባሉን ያስቃኛል።
    12 min
  • የየካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    130ኛው የአድዋ ድል በዓል በዛሬው ዕለት ተከበረ።
    በደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ግዛቶች ውስጥ በደረሰ ጥቃት 169 ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። በሥልጣን ክፍፍል ሂደት በፕሬዝደንቱና በተቀናቃኛቸው ኃይላት መካከል ግጭት መባባሱን የተመድ አመልክቷል።
    በመካከለኛው ምሥራቅ የተለኮሰው ጦርነት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። ኢራን እስራኤልን ጨምሮ በአቅራቢያዋ የአሜሪካ ይዞታ በሚገኝባቸው የአረብ ሃገራት ላይ ጥቃቷን ዛሬም አጠናክራለች። እስራኤልም በኢራን እና ሊባኖስ ላይ ድብደባዋን ቀጥላለች።
    የኢራን ጊዜያዊ አስተዳደር ምክር ቤት ኃላፊ የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተሳሳተ ስሌት ነው አሉ።
    10 min
  • የየካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በኬንያ ባጋጠመ የሄሊኮብተር መከስከስ አደጋ 6 ሰዎች መሞታቸውን የሐገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። እስራኤል በኢራን ላይ የጀመረችው ጥቃት ዛሬም አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን ኢራን በበኩሏ በእስራኤልና የአሜሪካ የጦር ሰፈር አላቸው ባለቻቸው የባሕረሰላጤው ሐገራት ላይ ጥቃት ፈፅማለች። በኢራን መልካም መፍትሔ የሚመጣው «ኢራን የኒኩሌር መርሃግብሯን ስትተው ነው» ሲሉ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ። የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን የኢራን ከፍተና መሪ አያቶላህ ኻመኒ ግድያን አወገዙ።
    8 min
  • የየካቲት 21 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናገሩ።
    • እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የተቀናጀ ጥቃት መፈጸም መጀመራቸውን አስታወቁ።
    • በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰውን መጠነ ሰፊ ጦርነት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ የተለያየ ምላሽ እየሰጠበት ይገኛል።
    • የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የአየር መንገድ ኩባንያዎች ወደ ቀጠናው የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ ሰርዘዋል።
    • ታሊባን የሚያስተዳድረው የአፍጋኒስታን መከላከያ ሚኒስቴር በሁለት የፓኪስታን የጦር ሰፈሮች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ።
    12 min
  • የአርብ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የየካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ኢትዮጵያና አዘርባጃን የመከላከያ ትብብር ሥምምነት ተፈራረሙ። ከትናንት ጀምሮ አዘርበጃንን የሚጎበኘዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የመሩት ከፍተኛ የባለሥልጣናት ልዑክ ከአዘርባጃን አቻዎቹ ጋር ከመከላከያ በተጨማሪ «በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ» የመግባቢያ ሥምምነት መፈራረሙን ዐቢይ አስታዉቀዋል።
    አማጺው M23 ቡድን ለቆ በወጣበት ምሥራቅ ኮንጎ ውስጥ የ171 ሰዎች አስከሬን በሁለት የጅምላ መቃብሮች ውስጥ መገኘታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ ።
    ኢራንን እንደምትደበድብ የምታስፈራራው ዩናይትድ ስቴትስ እጅግ አስፈላጊ ያልሆኑ የኤምባሲ ሠራተኞቿ ከእስራኤል እንዲወጡ ዛሬ ፈቀደች።
    12 min
  • የየካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብሔራዊ ምርጫ በ5 የምርጫ ክልሎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ "ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ" ትዕዛዝ ሰጠ። የኬንያ ፖሊስ ኬንያውያን ወጣቶችን ለሩስያ ጦር አባልነት ሲመለምል ነበር ያለውን ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ። በናይጀሪያ ሰሜን ምስራቃዊ ግዛት «እስላማዊ ጽንፈኞች» የተባሉ ታጣቂዎች በአንድ መስጂድ ውስጥ ስግደት ላይ በነበሩ ምዕመናን ፈጸሙት በተባለው ጥቃት 30 ሲሞቱ 3 መቁሰላቸውን ተሰማ።
    11 min
  • የየካቲት 18 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንት ፍቃዱን የሰረዘበት አዲስ ስታንዳርድ ሥራዉን አለማቋረጡን አስታወቀ።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ትናንት ባሰራጨዉ ደብዳቤ የአዲስ ስታንዳርድ የምዝገባ የምሥክር ወረቀት መሰረዙን አሰታዉቆ ነበር።-የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ያደረጉት ዓመታዊ የመርሕ ንግግር በአብዛኛዉ ሐሰትን ከዕዉነት የቀየጠ መሆኑን አጥኚዎችና ተንታኞች አስታወቁ።ትራምፕ በኢራን ላይ የሰነዘሩት ዛቻም ከቴሕራን ጠንካራ አፀፋ ገጥሞታል። --በግሪጎሪያኑ 2025፣129 ጋዜጠኞች መገደላቸዉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ CPJ አስታወቁ።አብዛኞቹን ጋዜጠኞች የገደለችዉ እስራኤል ናት።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ የካቲት 17 ቀን 2018
    አርስተ ዜና፤
    -የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በፊት እንዳይፀድቅ ውትወታ እያድረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ አስታወቀ።
    -ከያዝነዉ የፈረንጆቹ ዓመት 2026 መጀመርያ ጀምሮ በሁለት ወራት ጊዜ ዉስጥ ከአፍሪቃዉ ቀንድ አካባቢ ተነስተዉ ሜዲትራኒያን ባህር አቋርጠው ወደ አውሮጳ ለመግባት የሞከሩ ቢያንስ 606 ስደተኞች በባህር ሰጥመዉ መሞታቸውን IOM አስታወቀ።-ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ወረራ የጀመረችበት አራተኛ ዓመት ዛሬ በዩክሬይን መዲና ኪይቭ ላይ ታስቦ ዋለ። የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራትና ኔቶ ለዩክሬይን ጠንካራ አጋርነታቸዉን አሳይተዋል።
    11 min
  • የየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የፌዴሬሽን ምክር ቤት አምስት የምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ስምረት፣ ሳልሳይ ወያነ እና ባይቶናፓርቲ ተቃወሙ ።ከ3,000 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች በግብፅ ታስረው እንደሚገኙ ተገለፀ። ጀርመን ለዩክሬይን አጋርነቷን እንደምትቀጥል ገለፀች። ሃንጋሪ የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ያቀደውን ብድር አደናቀፈች። የዩናይትድ ስቴትስ በከባድ የክረምት የአየር ፀባይ የአስቸኳይ ጊዜ አወጀች።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…