የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የየካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    “ ኢትዮጵያ ሀይሏን የምትገነባው በቀጠናው ሽብር እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው “ ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ ፡፡ ከሶማሊያ በመነጠል ነጻነቷን ያወጀችው ሶማሌላንድ ለዩናይትድ ስቴትስ ማዕድንም ይሁን የጦር ሰፈር ለመስጠት ፍቃደኛ እንደሆነች አንድ የሶማሌላንድ ሚኒስትር ተናገሩ። የአሜሪካ የደህንነት አገልግሎት ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ቤት «ሊገባ ሞክሯል» ያለውን አንድ መሣሪያ የታጠቀ ግለሰብ ተኩሶ መግደሉን አስታወቀ።
    10 min
  • የየካቲት 14 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ክልል ውስጥ ወደ ሚገኙ የቀድሞ የጦር ሰፈሮቹ ይገባል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ «ሐሰት ነው » ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ።
    • እስራኤል በሊባኖስ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው የበካ ሸለቆ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ሦስት ሕጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
    • ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሁሉም ምርቶች ላይ ተጨማሪ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣሉ ።
    • ዩክሬን ሩስያ ውስጥ ጠልቃ በመግባት በፈጸመችው የድሮን ጥቃት በሚሳኤል ማምረቻ ኢንዱስትሪ ላይ ጉዳት ማድረሷ ተነገረ። በጥቃቱ 11 ሰዎች ቆስለዋል።
    11 min
  • የዐርብ የካቲት 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ እናት ፓርቲ "ለኢትዮጵያ" ወደተባለው የፓርቲዎች ቅንጅት መመለሱ ተገለጠ፤ ጄኔቭ፥ የተወሰኑ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር አዛዦች ለፍርድ መቅረብ አለባቸዉ-ተመድ፤ ሞቃዲሾ፥ ሶማሊያ ውስጥ በገንዘብ ችግር የምግብ ርዳታ ሊቋረጥ ይችላል ተባለ፤ ቤርሊን፥ የጀርመን መንግሥት የዶይቸ ቬለ የቱርኪዬ ዘጋቢ መታሰር እንደሚያሳስበው ገለጠ፤ ጅዳ፥ ሣዑዲ ዓረቢያ ከዩናይትድ ስቴትስ በቀረበላት የኑክሌር ስምምነት መሠረት ዩራኒየም ታበለጽግ ይሆናል፤ ኪዬቭ፥ ዩክሬን በሩስያና ቤላሩስ አትሌቶች የተነሳ በፓራሊምፒክ አልሳተፍ አለች
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ የካቲት 12 ቀን 2018
    አርስተ ዜና፤ ከኤፕስተን የወሲብ ቅሉሌት ጋር በተያያዘ የንጉሳዊ ማዕረጋቸዉን የተነጠቁት የብሪታንያ ንጉስ የቻርልስ ሳልሳዊ ታናሽ ወንድም ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ።-አንድ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬዚስ ጋዜጠኛ ወደ ትግራይ እንዳይበር መከልከሉን ዜና አገልግሎቱ ዛሬ ከቀትር በፊት ዘገበ።-የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲብ ጠይብ ኤርዶኻን በአዲስ አበባ ጉብኝታቸው ሶማሌላንድን እራሷን ሪፐብሊክ አድርጋ የገለፀች በማለት የሰጡትን ማስጠንቀቂያ የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አወገዘ።-ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ኬንያውያን በዩክሬን ከሩሲያ ጦር ጎን ቆመዉ ለዉግያ መጓዛቸዉ ተሰማ።
    14 min
  • የየካቲት 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሐገሪቱን ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ ዘመንን ለተጨማሪ 8 ወራት አራዘመ።-የቱርክ ፕሬዝደንት ሬሰፕ ጠይብ ኤርዶኻን የአፍሪቃ ቀንድ መንግሥታት ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት አሳሰቡ።ኤርዶኻን አዲስ አበባ ዉስጥ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ጋር ከተወያዩ በኋላ እንዳሉት የአፍሪቃ ቀንድ ተጨማሪ ግጭትና መከራ ሊደርስበት አይገባም።-የሩሲያና የዩክሬን ተደ,ራዳሪዎች ዤኔቭ-ስዊዘርላንድ ዉስጥ ያደረጉት ድርድር ያለዉጤት አበቃ።የሁለቱ ሐገራት ባለሥልጣናት ያደረጉትን ድርድር የሸመገሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ናቸዉ።
    10 min
  • የየካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የየካቲት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ክልል ኃይሎች በትግራይ ክልል ድንበር ላይ በብዛት እየሰፈሩ ነው ሲሉ አንድ ዲፕሎማት መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP ዘገበ። ማንነታቸውን ያልተገለጸው ዲፕሎማቱ «የፌደራሉ ሠራዊት ትግራይን ከቧል ፤« የትግራይ ክልል ኃይሎችም ድንበሮቻቸው ላይ እየሰፈሩ ነው» በማለት ተናግረዋል።
    የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ተይፕ ኤርዶሃን ዛሬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት 15 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና አንድ የምክር ቤት አባል ተናገሩ።
    12 min
  • የየካቲት 9 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በዋነኛው የኬንያው ጆሞኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ በተቀሰቀሰ የሥራ ማቆም አድማ በረራዎች ተስተጓጎሉ ። • የናይጄሪያ ጦር በቦርኖ ግዛት የተሰነዘረበትን የተቀናጀ የሽብር ጥቃት መመከቱን አስታወቀ። • የእስራኤል መንግሥት በምዕራባዊ የዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝ ሰፊ መሬት «የመንግሥት ንብረት» አድርጎ ለመመዝገብ የወሰነው ውሳኔ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀሰቀሰ። • ጀርመን በየብስ ድንበሮቿ ላይ የምታደርገውን ጥብቅ የስደተኞች እና የጸጥታ ቁጥጥር ለተጨማሪ ስድስት ወራት አራዘመች። • ሩሲያና በዩክሬንን ወደ ድ ለማምጣት ብቸኛዋ አቅም ያላት ሀገር አሜሪካ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ተናገሩ።
    11 min
  • የየካቲት 08 ቀን 2018 ዓ ም የዓለም ዜና
    39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጠናቀቀ።ባለፈው ጥቅምት ወር ሱዳን ውስጥ ከ6,000 በላይ ሰዎች በሦስት ቀናት ውስጥ ተገደሉ። የሙኒክ የጸጥታ ጉባኤ ተጠናቀቀ። የዩናይትድ ስቴትስ ህንድ ውቅያኖስ ላይ የነዳጅ መርከብ በቁጥጥር ስር አዋለች።ዩክሬን በሰው አልባ አይሮፕላን አንድ የሩሲያ ነዳጅ ማከማቻን አቃጠለች።
    10 min
  • DW Amharic የየካቲት 07 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በአፍሪካ “ግልጽ እና ድብቅ ግጭቶች ሥር እየሰደዱ” መምጣታቸውን “ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆኑ የመንግሥት ለውጦች” ማንሠራራታቸውን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ የባሕር በር ልታገኝ ይገባል የሚል አቋማቸውን ለ39ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ገልጸዋል።
    ስድስት የግል ባንኮች ድርሻዎቻቸውን በካፒታል ገበያ ለማስመዝገብ መቃረባቸውን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ይፋ አደረገ። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጆንጊሌ እና ምሥራቅ ኢኳቶሪያ ግዛቶችን ጨምሮ በመላ ደቡብ ሱዳን ግጭት መባባሱ እጅግ እንዳሳሰበው አስታወቀ።
    10 min
  • የየካቲት 6 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሮይተርስ የጋዜጠኖች ቡድን የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ እንዳይዘግቡ ፍቃድ መከልከሉን የዜና ወኪሉ አስታወቀ። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከጥር መጨረሻ ጀምሮ በከባድ የጦር መሣሪያ የታገዘ ግጭት መኖሩን ነዋሪዎች፣ ማኅበራት እና የዞኑ ፖሊስ ገለፁ። የኢራን መንግስት በሰላማዊ በሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን የሐይል እርምጃ የሚመረምር ገለልተኛ አጣሪ ቡድን አቋቋመ። አሜሪካ ሁለተኛዋ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ወደ መካከለኛ ምስራቅ እንደምትልክ ተሰማ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…