የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ከሰሞኑ በትግራይ ኃይሎች እና በፌዴራል መንግስቱ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ከተለያዩ ከተሞች የተፈናቀለው ህዝብ ቁጥር ከ60 ሺ በላይ መድረሱ ተገለጸ።
    • የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቬት ኩፐር ከአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ወደ ሀገሪቱ ለመድረስ የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እርምጃዎች ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን አስታወቁ ።
    • በኒጀር መዲና የአየር ኃይል የጦር ሰፈር ባለፈው ዓርብ ለደረሰው ጥቃት ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው በእንግሊዘኛ ምህጻሩ አይ ኤስ ኃላፊነት ወሰደ።
    • የናይጄሪያ ጦር ኃይል የጽንፈኛው ቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን አዛዥ መግደሉን አስታወቀ።
    11 min
  • የጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና ፤ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፤ህወሓት በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ሀይሎች መካከል ያለውን ችግር በንግግር ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን መግለፁ።ብሪታኒያ ፤በትግራይ ኃይሎች እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ዜጎቿ ወደ ሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን፣ እስራኤል በእስራኤ እና በሀማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ተከትሎ የራፋህ መሸጋገሪያ መንገድን በከፊል መክፈቷን፤ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንድ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ፍንጭ መስጠታቸውን፤ የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።
    9 min
  • የጥር 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የሶማሊያ እና የጂቡቲ መሪዎች ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ጋር ጂግጂጋ ውስጥ ተገናኙ ። • ትግራይ ክልል ውስጥ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት አንድ ሰው መገደሉ ተዘገበ። • በሰሜናዊ ናይጄሪያ ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድኖች በተለያዩ አካባቢዎች ባደረሷቸው ጥቃቶች ሲቪሎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገደሉ ። • ደቡብ አፍሪቃ እና እስራኤል አንዳቸው የሌላውን ከፍተኛ ዲፕሎማት በማባረር ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ተነገረ።
    10 min
  • የዐርብ ጥር 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ የሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት ያሳሰበው የአፍሪቃ ኅብረት የቅርብ ክትትል እያደረገ ነው፤ ቤርሊን፥ የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም የአዉሮጳ ሐገራት እንዲያግዙ የሱዳን ፖለቲከኞች ጠየቁ፤ ቤርሊን፥ የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም የአዉሮጳ ሐገራት እንዲያግዙ የሱዳን ፖለቲከኞች ጠየቁ፤ ናይሮቢ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኬንያ ውስጥ የጦር ሠፈር ልታስፋፋ ነው፤ ቴሕራን፥ የዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራንን ፍጥጫ ባየለበት በአሁኑ ወቅት እሥራኤል ድርድሩ ቢቀጥል ትሻለች ተባለ፤ ቪዬና፥ የተመድ የአውቶሚክ ተቆጣጣሪ ቦርድ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አደረገ
    11 min
  • የጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ከተሞች ያደርግ የነበረውን የዕለቱን በረራ ዛሬ ካቋረጠ በኋላ ስጋት እንዳደረባቸው የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ ። ነዋሪዎች በተለይ ለዶቼ ቬለ እንዳሉት በትግራይ እና በአጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች ግጭት መቀስቀሱ አሰሳስቧቸዋል።
    ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማሊያ የምትልከው የምግብ እርዳታ ላይ የጣለችውን እገዳ እንደምታነሳ አስታወቀች።
    የአውሮጳ ኅብረት በ15 የኢራን ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሉን ዛሬ አስታወቀ። ኅብረቱ ማዕቀብ ከጣለባቸው ውስጥ የአብዮታዊ ዘብ ፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት ዋና አዛዦችና ባለሥልጣናት ይገኙበታል።
    12 min
  • የጥር 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን በከፈተዉ ጥቃት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ያላቸዉን 80 ሰዎች መማረኩን አስታወቀ።መከላከያ ሠራዊት እንደሚለዉ በአካባቢዉ ሠላም እየሰፈነ ነዉ።---የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን ለመደብደብ አሁንም እየዛቱ ነዉ።ኢራን ለአፀፋ መዘጋጀትዋን አስታዉቃለች።---የጀርመን ናዚ በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት የጨፈጨፋቸዉ አይሁድና ሌሎች የአናሳ ዝርያ ተወላጆች ዛሬ በበርካታ ሐገራት ታሰቡ።የጀርመን ምክር ቤት ፕሬዝደንት እያንሰራራ የመጣዉን የአይሁድ ጥላቻ ለማስወገድ ጀርመን ልዩ ኃላፊነት አለባት ብለዋል።
    12 min
  • የጥር 19 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክርስቶፎር ላንዳው እና በአፍሪቃ የአሜሪካ ጦር ዕዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን በኢትዮጵያ አየር ኃይል የአቪዬሽን 90ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኙ።
    • ብሔራዊ ምርጫ ቤርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ባዘጋጀው የመራጮች እና የዕጩዎች ምዝገባ ሥርዓት ላይ "የዕጩዎች የኢ-ሜል አድራሻ አስገዳጅ መሆን እንደሌለበት በመታሙኑ በአማራጭ እንዲሞላ መደረጉን" ገለፀ።
    • በስደተኞች ላይ ከፍተኛ ስቅየት የታከለበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተከሰሰው ኤርትራዊ ዛሬ ኔዘርላንድስ ውስጥ በአይነቱ ልዩ ነው የተባለ ችሎት ላይ ሊቀርብ ነው
    12 min
  • የጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜናየኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ «ለተከታታይ 42 ቀናት አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ባለመኖሩ የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ከቫይረሱ ነፃ መሆናችንን አረጋግጠናል ሲሉ ዛሬ ተናገሩ።
    ሰሜን ምሥራቅ ኬንያ በሚገኘው ሁሉጎ በተባለው ስፍራ አልሸባብ አንድ የአካባቢው ማኅበረሰብ መሪ እና አንድ መምህር መግደሉን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ።
    ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች መርጃ ድርጅት በምህጻሩ IOM በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በሜዴትራንያን ባህር ላይ በጉዞ ላይ ከነበሩት መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ወይንም ሳይሞቱ እንዳልቀረ አስግቷል።
    12 min
  • የጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና፤በደቡብ ሱዳን ዳግም የተከሰተው ግጭት ከ180,000 በላይ ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉን፣በዩናይትድ ስቴትስ ከ 600,000 በላይ ደንበኞች በክረምት አውሎ ንፋስ ምክንያት የኤለክትሪክ ኃይል ማጣታቸውን እና ከ10,000 በላይ የሚሆኑ ለዛሬ እሁድ የታቀዱ በረራዎችም መሰረዛቸውን፣ኢራን በተፈጠረው አለመረጋጋት በሁለት ቀናት ውስጥ 30,000 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል መባሉን፣በኢራን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት፣ ተመራጭ አይደለም ስትል ፈረንሳይ ማስታወቋን እንዲሁም በዩክሬን ጦርነት እንዲቆም የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጥሪ ማቅረባቸውን ይስቃኛል።
    10 min
  • የጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ ጋር ከትብብር ውጭ የሚያስቡ ያሏቸውን አካላት አስጠነቀቁ ።
    • የአሜሪካው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክርስቶፎር ላንዳው ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ በቀጣናው ሃገራት ጉብኝት ለማድረግ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
    • የዩጋንዳ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ ፓርቲ መሪ ኪዛ ቢስጊዬ በእስር ቤት ውስጥ ተገቢው ህክምና መነፈጋቸውን ባለቤታቸው ይታወቅልኝ አሉ ።
    • የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጸረ ስደተኞች ዘመቻ በበረታባት የሚኒሶታ ግዛት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የመንግስትን ዘመቻ ለመቃወም አደባባይ ወጡ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…