የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥር 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለት የቱርኪዬ ዜጎች እና አንድ ኢትዮጵያዊ "ባልታወቁ" ታጣቂዎች ተገደሉ።
    • ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ለመስክ ስራ የወጡ የቴሌኮም ሰራተኞች በታጣቂዎች መታገታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።
    • የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ገዢ የብልጽግና ፓርቲ «አጀንዳ ቀርጾ ህዝቡን ወደ ሁከት ለማስገባት ጦርነት አውጇል » በማለት ወነጀሉ።
    • በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ትናንት ሰኞ በደቡብ ምስራቃዊዋ የሲንጃ ከተማ በፈጸመው የድሮን ጥቃት 27 ሰዎች ተገደሉ ።
    • በመንግስት የተቃዉሞ አመጽ እና ድጋፍ መሃል እየተናጠች በምትገኘው ኢራን የሟቾች ቁጥር 646 መድረሱ ተነገረ።
    12 min
  • የጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አዲስ የሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ግንባታ የአከባቢው ማህበረሰብ ላይ ስጋትን ደቅኗል አሉ፡፡ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሥደተኞችን የመርዳት የሞራል፣ የሰብአዊነትና የሕግ» ኃላፊነት እንዳለበት አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) የበላይ ኃላፊ አስታወቁ። ኢራን ለጦርነትና ለሰላማዊ ውይይት ለሁለቱም ተዘጋጅቻለሁ አለች።
    13 min
  • የጥር 3 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ወደ ጂቡቲ አቅንተው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌህ ጋር ተነጋገሩ ።
    • ቻይና ፣ሶማሊያ ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች።
    • የሱዳን ብሔራዊ ጦር መንግስታዊ መቀመጫ በስደት ላይ ከነበረበት ወደ መዲናዪቱ ካርቱም ተመለሰ።
    • አሜሪካ ተቃዋሚዎችን ወግና በኢራን ላይ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ እስራኤል እና የአሜሪካ ወታደሮች ዒላማዋ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠነቀቀች ።
    • አሜሪካ ፍሎሪዳ ባስተናገደችው 46ኛው የአለም አገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለተኛነት አጠናቀቀች ።
    8 min
  • የጥር 2 ቀን 2018 ዓ ም የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያ ውስጥ "ፌደራል ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ" የተባለ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት በምሥረታ ላይ መሆኑን ፖለቲከኛ ደስታ ዲንቃ ዛሬ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ።
    በኢራን በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ መንግሥት ማብረዱን አስታወቀ።
    ለቀናት ከዘለቀ ውጊያ በኋላ የሶሪያ ጦር አሌፖን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ።
    የኩርድ ተወካዮች ግን ይህን አጣጥለው ውጊያው ቀጥሏል ብለዋል።
    የጋዛ ሰርጥ ነዋሪዎች ሁኔታ በዚህ በክረምት ወቅት ይበልጥ መባባሱን የጀርመን ቀይ መስቀል ድርጅት አስታወቀ።
    ሩሲያ እና ዩክሬን ሌሊቱን አንዳቸው ሌላቸው ላይ የድሮን ጥቃቶች ሰነዘሩ
    የጂ7 ጉባኤ ለትራምፕ ልደት ሲባል አንድ ቀን ተገፋ።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥር 1 ቀን 2018 አርብ
    አርስተ ዜና፤
    --በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የሚደገፈው የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት የተሰኘው የደቡብ የመን ተገንጣይ ቡድን መፍረሱን አስታወቀ። የቡድኑ መሪ ከቀናት በፊት ከየመን በባሕር ወደ ሶማሌላንድ በመጓዝ ከዚያ በአውሮፕላን ወደ አቡዳቢ መግባታቸውን ሳውድ አረቢያ መግለጻ ይታወሳል። --ትግራይ ክልል በኢኮኖሚ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ እና ፀጥታ ስጋት ዉስጥ መሆንዋ ተነገረ።--የአዲሱ የቬንዙዌላ ጊዜያዊ አስተዳደር በማዶሮ ዘመን እስር ላይ የነበሩ በርካታ ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞችን ለቀቀ።--ኢራን ዉስጥ በተከሰተዉ የኑሮ ውድነት ምክንያት የተነሳዉ ፀረ መንግሥት ተቃዉሞ ዛሬም ተባብሶ እንደቀጠለ ነዉ።
    11 min
  • የታኅሣሥ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ባለፉት ሁለት ሳምንታት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን በምሥራቅ መሥቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸው፤ ሌሎች 10 ደግሞ መቁሰላቸው ተነገረ።
    በሳዑዲ አረቢያ የሚታደኑት የደቡብ የመን ተገንጣይ ቡድን መሪ አይደሩስ አል ዙበይዲን ከየመን በድብቅ ወደ አቡዳቢ መዉሰዳቸዉ ተሰማ።
    ቻይና ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፍ የባሕር ቀጣና የሌሎች ሃገራትን መርከቦች በዘፈቀደ መያዟ ዓለም አቀፍ ሕግ የጣሰ ነው ስትል ኮነነች።
    ኢራን ውስጥ የኤኮኖሚ መዳከም የቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ በመላው ሀገሪቱ መዳረሱ እየተነገረ ነው።
    14 min
  • የዓለም ዜና፤ ታኅሣሥ 29 ቀን 2028 ረቡዕ
    አርስተ ዜና --አሜሪካ ከቬንዙዌላ ነዳጅ ጋር ግንኙነት ያለው የሩስያ ባንዲራን ያነገበ የነዳጅ ጫኚ መርከብ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ መያዝዋን አስታወቀች። የአሜሪካ ጦር ሌላ የካሪቢያን ባህር ጫኝ መርከብንም በቁጥጥር ስር አውሏል። በሌላ በኩል ትራምፕ የቬንዙዌላ "ጊዜያዊ አስተዳደር" እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለአሜሪካ እንደሚያስረክብ አስታወቁ።--በኢትዮጵያ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በድምቀት እየተከበረ ነዉ።--ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች "አንዳቸው የሌላኛቸውን ሰላም እና ደኅንነት" እንዲሁም "የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ" ያላቸውን ስልታዊ አጋርነት በድጋሚ ማረጋገጣቸዉ ተሰማ።
    13 min
  • የታኅሣሥ 28 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የእስራኤል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ሰዓር ራስዋን የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ብላ የምትጠራዉን ግዛት ጎበኙ።ሶማሊያ የእስራኤሉን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጉብኝትን «ሕገ-ወጥና ዋጋ ቢስ» በማለት አዉግዛዋለች።--የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የቬኑሱዌላዉን መሪና ባለቤታቸዉን ማገታቸዉን የቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ዛሬ እንዳለዉ የአሜሪካ ርምጃ «ጉልበተኞች የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ የሚል መልዕክት ያስተላልፋል።» -የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ግሪላንድን ከዴንማርክ ለመንጠቅ በድጋሚ መዛታቸዉን ሰባት የአዉሮጳ ሐገራት መሪዎች ተቃወሙት።
    12 min
  • የታኅሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የኢራን የፍትሕ ሚኒስትር በሐገሪቱ ሰልፍ በሚያካሂዱት ላይ በቸልታ እንዳማያልፉ አስጠነቀቁ። የቀድሞው የሩስያ ፕረዚደንት ዲሜትሪ ሜድቪዴቭ፤ «የጀርመን መራሔ መንግስት ፍሬደሪሽ ሜርስም እንደ ቬንዙዌላው ፕረዚደንት በተመሳሳይ ወታደራዊ ዘመቻ ሊታገቱ ይገባል» ሲሉ የሰጡትን አስተያየት በርሊን በጥብቅ አወገዘች። ዩናይትድ ስቴትስ እንደ ዓለም ዳኛ ሆና እየተንቀሳቀሰች ነው ሲል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሰ።
    12 min
  • የታኅሳስ 26 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በናይጄሪያ ማዕከላዊ ኒጀር ግዛት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች ተገደሉ • የየመን ተገንጣይ ቡድን በትንሹ 80 ያህል ወታደሮቼ ተገድለዉብኛል አለ። •በአሜሪካ ወታደሮች ተይዘው የተወሰዱት የቬንዙዌላው ፕሬዚደንት ኒኮላስ ማዱሮ የዕጽ ዝውውር የሽብር ወንጀል ክስ ሊመሰረትባቸው ነው። • ሩስያ በአውሮጳዉያኑ አዲስ ዓመት ሰሞን በዩክሬን ላይ ከ2000 በላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን ፕሬዚዳንት ቮልዶሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ። • ጀርመን ውስጥ ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ።
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…