የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የታኅሣሥ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ የፀጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው የክልሉ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ ገደብ ከዛሬ ምሽት ሁለት ሰዓት ጀምሮ መጣሉ ተገለጸ።
    ዩናይትድ ስቴትስ አራት አዲስ ዓለም አቀፍ የጤና የመግባቢያ ስምምነቶችን ከአራት የአፍሪቃ ሃገራት ጋር ተፈራረመች።
    በቱርክ አንካራ አቅራቢያ በተከሰከሰ አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ የሊቢያ ጀነራሎች እና የልዑካን ቡድናቸው ሕይወት ማለፉ ተነገረ። ሦስቱ የበረራ ሠራተኞችም አልተረፉም።
    ዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽነርን ጨምሮ በአምስት አውሮጳውያን ላይ የጣለችውን የቪዛ እገዳ የአውሮጳ ሕብረት፤ ጀርመን እና ፈረንሳይ አወገዙ።
    12 min
  • የታሕሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን ሀገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ በምርጫ አስቻይ ኹኔታ እና መሠል ጉዳዮች ላይ ትናንት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።የየመን ሁቲ አማጽያንና በአለም አቀፉ ማሕበረሰብ ቅቡልነት ያለውና አሁን የመንን እየመራ ባለው መንግስት መካከል በተደረገው ድርድር ከሁለቱም በኩል ወደ 3,000 የሚሆኑ የጦር እስረኞችን ለመልቀቅ ተስማሙ።ንብረትነቱ የሜክሲኮ የባሕር ሐይል የሆነና ለሕክምና አገልግሎት የሚንቀሳቀስ አንስተኛ አውሮፕላን ዛሬ ተከስክሶ ቢያንስ 5 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።
    12 min
  • የታኅሣሥ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) በትግራይ ክልል መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ወገኖች ለረሀብ መጋለጣቸውን አመለከተ። በረሀብ ላይ ለሚገኙት ወገኖች መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት፤ የተፈናቀሉትም ወደ የቀያቸው መመለስ እንዳለባቸውም አሳስቧል።
    የናይጀሪያ መንግሥት በቅርቡ ታግተው ከነበሩ የቀሩትን 130 ልጆች ማስለቀቁን አስታወቀ። በዛሬው ዕለት ቤተሰቦቻቸውን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
    በዛሬው ዕለት በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በተከሰተ የቦምብ ፍንዳታ አንድ የሀገሪቱ ጀነራል ተገደሉ።
    ኢራን የሚሳኤል መርኀግብሯ መከላከያ እና የሚቃጣባትን ጥቃት ለማስቆም የተነደፈ መሆኑን አሳሰበች።
    12 min
  • የታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ወደ ጋምቤላ በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ ኢሰመኮ አሳሰበ ፤ ደቡብ አፍሪቃ ፤ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች በታጣቂዎች ጥቃት ተገደሉ ፤ የእስራኤል ካቢኔ እስራኤል በኃይል በያዘችው የፍልስጤም ግዛት የዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ 19 አዳዲስ የሰፈራ መንደሮች እንዲቋቋሙ አፀደቀ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ከቬንዙዌላ የባህር ዳርቻ ለሁለተኛ ጊዜ ድፍድፍ ዘይት የጫነ መርከብ በቁጥጥሯ ስር አዋለች፤
    9 min
  • DW Amharic የታኅሳስ 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ዒድሪስ ጦርነት በሚካሔድባቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ሌሎች ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ወደ ኒው ዮርክ አቀኑ። የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ቦላ ቲኑቡ የሀገራቸውን የጸጥታ ተቋማት በከፍተኛ ሁኔታ ለማጠናከር ቃል ገቡ። አንድ ኤርትራዊን ጨምሮ አራት ሰዎች ባለፈው አንድ ሣምንት በዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት እና የጉምሩክ መስሪያ ቤት በእስር ላይ ሳሉ መሞታቸውን የሀገሪቱ መንግሥት መረጃ ይፋ አደረገ። የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ ከጎርጎሮሳዊው 2028 በኋላ በየአራት ዓመቱ እንደሚካሔድ ተወሰነ።
    10 min
  • የታኅሳስ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ማሕሙድ በአዲስ አበባ ተገናኙ። በኢትዮጵያ ለስደተኞች የሚደረገው ድጋፍ ከውድቀት አፋፍ እንደሚገኝ መንግሥት እና አራት ድርጅቶች አስጠነቀቁ። በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ ሊባባስ እንደሚችል የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባልደረባ ሥጋታቸውን ገለጹ። ስዊድን በኤርትራ ላለፉት 24 ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅ በሕይወት እንዳለ ገለጸች። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች ሀገር ዜጎች ቋሚ የአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ በዕጣ የሚያገኙበትን የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራም ሊያቆም ነው።
    12 min
  • የሐሙስ ታኅሣሥ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ጋምቤላ፥ ከፖሊስ አዛዥ ግድያ በኋላ በከተማዪቱ ሥጋቱ እንዳየለ ነው፤ አጣዬ፥ የአማራና ኦሮሞ ማኅበረሰብ ሰላም በማውረድ በጋር ማረስና መሥራት ጀመሩ፤ ዋጋዱጉ፥ቡርኪና ፋሶ በቁጥጥር ስር አውላቸው የነበሩ 11 የናይጄሪያ አየር ኃይል አባላትን ለቀቀች፤ ዋሽንግተን፥ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በደቡብ አፍሪቃ መታሰራቸውን የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አወገዘ፤ ብራስልስ፥ በአውሮጳ ኅብረት ጉባኤ የታገደው የሩስያ ሐብት ዋነኛው አጀንዳ ነው፤ ኪዬቭ፥ በጎርጎሪዮሱ 2026 እስከ 50 ቢሊዮን ዩሮ የበጀት ክፍተት እንዳለባት ዐሳወቀች
    10 min
  • የታኅሣሥ 8 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    • የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉ ተፈጻሚ አለመሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ለቀጠለው ግጭት አንዱ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ።
    • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወይም በእንግሊዘኛ ምህጻሩ አር ኤስ ኤፍ በዳርፉሯ የኤል ፋሽር ከተማ የጅምላ ጭፍጨፋ እና የአካል ማጉደል ተግባር መፈጸሙን የሚያረጋግጥ አዲስ ዘገባ ይፋ ሆነ።
    • የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጥኤማዉያንን ጨምሮ ከሰባት በላይ ሃገራት ላይ የጉዞ ዕቀባ ጣሉ።
    • በአውስትራሊያ የቦንዲው የባሕር ዳርቻ ጥቃት የተጠረጠረው ግለሰብ 15 የግድያ ክሶችን ጨምሮ በ59 ወንጀሎች ክስ ተመሰረተበት ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ታሕሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
    አርስተ ዜና፤ --ኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ረቡዕ በሚያካሂደዉ የጋራ ስብሰባ የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ንግግር እንደሚያደርጉ ታወቀ። ሞዲ መዲና አዲስ አበባ ገብተዋል።--ሱዳን በድጋሚ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ቀዉስ መዘርዝር ቀዳሚ የዓለም ሃገር መሆንዋ ተገለፀ። ከሱዳን ቀጥሎ የፍልስጤም ግዛቶች ፤ኢትጵያና ሄይቲ በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ቀዉስ መዘርዝር 3ኛ ደረጃ ላይ በየተራ ተቀምጠዋል።--በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም እየተካሄደ ያለዉ ዉይይት እና ድርድር ፤ ለሰላም «ከምንጊዜውም በላይ ቅርብ ሆንዋል» ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
    11 min
  • የታሕሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዳሰነች ወረዳ መስተዳድር ለሁለተኛ ጊዜ የሕዝብ እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታወቀ ፡፡ኤርትራ ያለፍርድ ያሰረቻቸውን ወደ 10,000 የሚገመቱ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ሳውዲ አረቢያ በመገባደድ ላይ ባለው ጎርጎሮሳዊ 2025 ዓመተ ምህረት የሞት ቅጣት በመፈጸም የዓለም ክብረወሰን መያዝዋን ዘገባዎች አመላከቱ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…