የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የታሕሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በሱዳን በምትገን የዲሊንጅ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 7 ስቪሎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ። የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ «በኢራን ይደገፋል» ያለው የሒዝቦላህ አባላት ናቸው ያላቸውን 3 ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ። በአውስትራልያ ቦንዲ በተበለ የባሕር ዳርቻ 2 ጠመንጃ የታጠቁ ግለሰቦች ዘመናት ያስቆጠረውን ባሕላዊ ክብረበ ዓላቸውን ሲያከብሩ በነበሩ ይሁዲዎች ላይ ዛሬ በፈጸሙት የተኩስ እሩምታ ቢያንስ 12 ሰዎች መሞታቸውን ተሰማ።
    9 min
  • DW Amharic የታኅሳስ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ እና የኤርትራ “ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር” ብሪታኒያ እና ቱርክን ጨምሮ አምስት ሀገራት በጋራ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ ሀገራት “ማንኛውንም ውጥረት ወይም አለመግባባት በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ” የአውሮፓ ኅብረት ጠይቋል። ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት አባልነት ራሷን ለማግለል ያሳለፈችው ውሳኔ እንዳሳዘናት ጅቡቲ አስታወቀች። ርዋንዳ በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወሰደችው እርምጃ በዶናልድ ትራምፕ አሸማጋይነት በዋሽንግተን የተፈረመውን የሰላም ሥምምነት እንደሚጥስ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አስታወቁ።
    9 min
  • የዓለም ዜና ታህሳስ 3 ቀን 2028 አርብ
    -ዶይቸ ቬለ (DW) ሁለት ዘጋቢዎቹ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በቋሚነት መታገዳቸውን አጥብቆ ተቃወመ። ሰባቱ ጋዜጠኞች ስራቸዉን ቀጥለዋል።
    -ኢትዮጵያና ኤርትራ አንዳቸው የሌላውን የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ የተመድ አሳሰበ። በሁለቱ ሀገራት መካከል“እንደገና የተቀሰቀሰዉ አዲስ ውጥረት” እንዳሳሰበውም ገልጿል። በሌላ በኩል ኤርትራ እራስዋን ከኢጋድ አባልነት አገደች።-የትራምፕ አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ህጋዊ መኖርያ ፈቃድን በግዚያዊነት ማገዱን አስታወቀ።-ጀርመን በሰሜን ኢትዮጵያን ለሰላም ግንባታ፣ ለማረጋጋት እና ለግጭት መከላከል ጥረቶች የሚውል ተጨማሪ የ5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገች።
    13 min
  • የታኅሣሥ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ጋዜጠኛ እዮብ ሽመልስ በአስቸኳይ እንዲፈታ CPJ ጠየቀ፤ ከ400 በላይ ንፁሀን ዜጎች በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተገደሉ፤ ዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ ሱዳንን መንግሥትን አስጠነቀቀች፤ በክሮኤሺያ-ቦስኒያ ድንበር አቅራቢያ ጀልባ ሰምጣ ሶስት ስደተኞች ሞቱ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ነዳጅ የጫነች የቬንዙዌላ መርከብ በቁጥጥሯ ስር አዋለች፤በዩክሩን ሰው አልባ አይሮፕላኖች የሩሲያ አይሮፕላን ማረፊያዎች ስራ ተስተጓጎለ
    11 min
  • የታኅሣሥ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር የቀድሞ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ የ13 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው።
    በዓለም የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የሚውለው የገንዘብ ድጋፍ እየቀነሰ፤ ፀረ መብት ለሆኑ እንቅስቃሴዎች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ እየጨመረ መሆኑን የተመድ አመለከተ።
    ሩዋንዳ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ቡሩንዲ ሆን ብለው የሰላም ስምምነቱን እየጣሱ ነው ስትል ከሰሰች። ዴሞክራቲክ ኮንጎ በበኩላ ዩናይትድ ስቴትስ ሩዋንዳን አደብ ታስገዛልኝ ብላለች።
    ሩሲያ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከምዕራብ ሃገራት መሪዎች ብቸኛው የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ የሚገዳቸው መሪ ናቸው አለች።
    12 min
  • የማክሰኞ ኅዳር 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    ኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና መመረጧ፤
    ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት አፋሀድ ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ የተደረገ ቃለ መጠይቅ ፤
    ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የመጪውን ምርጫ ቀን ይፋ ማድረጉ
    20 min
  • የማክሰኞ ኅዳር 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አፋሕድ ከመንግስት ጋር ተደራደረ መባሉን የድርጅቱ ዋና ሰብሳቢ አቶ እስክንድር ነጋ ውድቅ አደረጉ፤ አ.አ፥ በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚከናወንበት ቀን ይፋ ሆነ፤ ፓሪስ፥ በጎርጎሪዮሱ 2025 በርካታ ጋዜጠኞችን በመግደል እሥራኤል ቀዳሚ ናት፤ ሞቃዲሹ፥ ሶማሊያ ውስጥ ድርቅ በዐሥር ሺህዎችን ለስደት መዳረጉ ተገለጠ፤ ኪዬቭ፥ ዩክሬን እና የአውሮጳ ኅብረት የተጣራ የሰላም እቅድ ለአሜሪካ እንደሚያቀርቡ ዐሳወቁ፤ ኮሎኝ፥ አንጋፋው ጋዜጠኛ ቦጋለ መኩሪያ ከዚህ ዓለም በ85 በሞት ተለየ፤
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 29 ቀን 2018 ሰኞ
    አርስተ ዜና፤ የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሃን ቫዴፑል የቻይና መንግስት በዩክሬን ያለውን ጦርነት እንዲያቆም ሩሲያ ላይ ጫና እንዲያደርግ ጠየቁ። ቻይናን የሚያህል በሩሲያ ጫና ሊያደርግ የሚችል ሌላ ምንም አይነት ነገር የለም ሲሉ ቫዴፑል ወደ ቤጂንግ ከማቅናታቸዉ በፊት ተናግረዋል። የ20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሆሳዕና ከተማ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በደማቅ ተከበረ። በሚቀጥለዉ ዓመት እለቱን ጅማ ከተማ እንድታስተናግድ ተመርጣለች። የሶሪያው አምባገነን በሽር አል አሳድ ከስልጣን ከተወገዱ ዛሬ አንድ ዓመት ሞላቸዉ። በሱዳን የሰው አልባ አውሮፕላን 63 ህጻናትን ጨምሮ 114 ሰዎች ተገደሉ።
    15 min
  • DW Amharic የኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና፤ በቤኒን መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን እስራኤል ከሃማስ ጋር ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እደምትሸጋገር መገለፁን፣ጀርመን በእስራኤል ታሪካዊ ሃላፊነት አለባት ሲሉ መራሄ መንግስት ፍሬድሪሽ ሜርዝ መግለፃቸውን፣ እንዲሁም ሩሲያ ፤በዩክሬን ክሬሜንቹክ ከተማ የአየር ጥቃት መፈፀሟ የሚያስቃኙ ዜናዎችን አካቷል።
    8 min
  • DW Amharic የኅዳር 27 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ መካከል “አዲስ ግጭት እንዳይቀሰቀስ መከላከል” ላይ ማተኮር እንዳለባት የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይፋ ያደረገው የብሔራዊ ደሕንነት ፖሊሲ ሰነድ አሳየ። ኢትዮጵያ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በድሮን በፈጸመው ጥቃት 33 ሕጻናትን ጨምሮ 50 ሰዎች መገደላቸውን የሐኪሞች ቡድን አስታወቀ። በደቡብ አፍሪካ በርካታ ተጠርጣሪዎች በከፈቱት ተኩስ ሕፃናትን ጨምሮ 11 ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ ገለጸ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ወደ እስራኤል እና ዮርዳኖስ አመሩ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…