የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ዶይቼ ቬለ ፈቃዳቸው የተሰረዘ ሁለት ዘጋቢዎቹን ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጥያቄ አቀረበ።
    የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ልጅ የሆኑት የሀገሪቱ ጦር ኃይል ኃላፊ ከምርጫ ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 30 ሰዎች መገደላቸውን፤ ከሁለት ሺህ በላይ ደግሞ መታሠራቸውን አስታወቁ። የተመድ የዩጋንዳ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገልጿል።
    ኢራን ውስጥ ከአምስት ሺህ በላይ ተቃዋሚዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የመብት ተሟጋቾች አመለከቱ።
    ዳቮስ ስዊዝርላንድ በተካሄደው የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ አሳሳቢ የዓለም ችግሮች ችላ ተብለዋል ተባለ።
    13 min
  • የሐሙስ ጥር 14 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ዳቮስ፥ ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያና ግብፅን ለመሸምግል ማቀዳቸዉን ዐሳወቁ፤ አዲስ አበባ፥ የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ተነጋገሩ፤ ካርቱም፥ የሱዳን ጦርነት በአገሪቱ የትምህርት ቀውስ መፍጠሩን ለጋሾች ዐሳወቁ፤ ዳቮስ፥ «የዓለም ሥርዓት ትንፋሽ በሚያሳጣ መልኩ እየተሰነጣጠቀ ነው»፦ ፍሬድሪሽ ሜርትስ፤ ቤርሊን፥ ጀርመን በአገር ስለላ ተሳተፉ ያለቻቸውን አንድ የሩስያ ዲፕሎማት ከአገር አባረረች፤ አንካራ፥ የቱርክ እና የኢራን ፕሬዚደንቶች ስለ ወቅታዊ ጉዳይ በስልክ ተወያዩ
    10 min
  • የጥር 13 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የጀርመን የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዮሐን ቫደፉል ኬንያንና ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ዛሬ ናይሮቢ ገብተዋል።የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በተለይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በሚያደርጉት ዉይይት የትግራይን ዉጥረትና የኢትዮጵያንና የኤርትራን አለመግባባት እንደሚያነሱ አስታዉቀዋል።---የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሐገራቸዉ ግሪንላንድን ለመወስደት ኃይል እንደማትጠቀም አስታወቁ።ግሪንላንድን ለመዉሰድ ግን በድጋሚ ዝተዋል።-----ቻይና፣ ምያንማርና እስራኤል ባለፈዉ የግሪጎሪያኑ ዓመት 2025 ከዓለም ሐገራት ሁሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ጋዜጠኞች ማሰራቸዉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታወቀ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥር 12 ቀን 2018 ማክሰኞ
    --የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን ህብረቱ ግሪንላንድ ውስጥ “ግዙፍ” መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ማቀዱን ተናገሩ። ኮሚሽነርዋ ይህን የተናገሩት ትራምፕ የአርክቲክ ውቅያኖስ ደህንነትን ለማስጠበቅና ግሪንላንድን ለመጠቅለል ዛቻ እያደረሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት ነዉ።--የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኧል ሲሲ ዳቮስ ስዊዘርላንድ ላይ እየተካሄደ ባለዉ የዓለም ኤኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝተዉ እንደሚነጋገሩ አስታወቁ።--ሩሲያ በዩክሬይን መዲና ኪየቭ ላይ ባደረሰችዉ የአየር ላይ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ህንፃዎች የኤሌትሪክ ኃይልና የውኃ አቅርቦት ተቋረጠ።
    13 min
  • የጥር 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በዛሬው ዕለት በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ።
    የተመድ በያዝነው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2026 የመን ውስጥ ሰብአዊ ቀውስ ሊባባስ እንደሚችል ከወዲሁ አሳሰበ።
    የሊቢያ የፀጥታ ባለሥልጣናት በድብቅ እስር ቤቶች ተይዘው የቆዩ ከ200 በላይ ስደተኞችን ነጻ ማውጣታቸው ተነገረ። አብዛኞቹ ስደተኞች ከሶማሊያ እና ኤርትራ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል።
    በግሪንላንድ ጉዳይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት የአውሮጳ ሃገራት ላይ የዛቱት የቀረጥ ጭማሪ የአትላንቲክ ማዶ ለማዶ ትስስርን ሊጎዳ እንደሚችል የአውሮጳ ኮሚሽን አሳሰበ።
    12 min
  • የጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ግብፅ እና ሱዳን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ሀሳብ አወደሱ፤የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የከተራ በዓልን በድምቀት እያከበሩ ነው፤ኡጋንዳ የኢንተርኔት አገልግሎት በከፊል መስራት ጀመረ፤ በኢራን ፀረ መንግሥት ተቃውሞዎች እስከ 18,000 የሚደርሱ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀረም፤የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ
    10 min
  • የጥር 9 ቀን፤ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለአንዴና ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል ግብጽ እና ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ድርድር ለማስገባት አገራቸው አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ፡፡ የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራም የግብፁ ፕረዚደንት ዓብደልፋታሕ አልሲስን የጋዛ የሰለም ቦርድ አድርገው ማጨታቸውን ታውቋል።የ81 አመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ ሐሙስ ዕለት በተካሄደም ምርጫ ማሸነፋቸውን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረገ። ሩስያ ሌሊቱን ለዛሬ አጥቢያ በዩክሬይን ግዛት በፈጸመችው ጥቃት አንድ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋም ማውደሟን ናፍቶ-ጋዝ የተባለ የግል ኩባንያ አስታወቀ።
    11 min
  • የጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ከሑመራ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች “ደሕንነታቸው ተጠብቆ በክብር፣ መረጃ ኖሯቸው እና በፈቃደኝነት” ወደ ቀያቸው መመለስ መጀመር አለበት የሚል አቋም አሜሪካ እንዳላት በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ተናገሩ። • በዩጋንዳ ትናንት ሐሙስ በተደረገው እና ዛሬ ውጤቱ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተቀሰቀሰ ተቃዉሞ በትንሹ አስር ሰዎች ተገደሉ። • አዲሱን የጋዛ የሽግግር አስተዳደር ስራ የሚቆጣጠር ዓለማቀፍ ተቆጣጣሪ ቦርድ ማቋቋማቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናላድ ትራምፕ አስታወቁ። • በኢትዮጵያ የፊልምና የመዝናኛ ዘርፍ እውቁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
    12 min
  • የጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ስምንት ፓርቲዎች ሀገራዊ ምክክር በክልሉ እንዲካሄድ ለማገዝ ተስማሙ። ሐማስ በአሜሪካ ተነሳሽነት የተጀመረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ክፍል አካል የሆነውን በፍልስጤም ይቋቋማል የተባለውን የባለሙያዎች ኮሚቴ እንደሚቀበለው አስታወቀ። የጀርመን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የጀርመን አውሮፕላኖች በኢራን የአየር ክልል እንዳይጠቀሙ አሳሰበ። የአውሮፓ ሕብረት አባል ሐገራት ወታደሮቻቸውን የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እጠቀልላታለሁ ወዳሏት ግሪንላንድ መላክ ጀመሩ።
    11 min
  • የረቡዕ ጥር 6 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ጁባ፥ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከፍተኛ ልዑካን ተወያዩ፣ ሞቃዲሾ፥ ሶማሊያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የነበራትን ስምምነት ሙሉ በሙሉ አቌረጠች፣ባማኮ፥ የነዳጅ እጥረት በማሊ በረራ እንዲሰረዝ አስገድዷል፣ ፓሪስ፥ ፈረንሳይ ግሪንላንድን በተመለከተ የትራምፕ አስተዳደር የሰጠውን ቀስተያየት በቀላሉ ዐታየውም፣ቴሕራን፥ የኢራን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰልፈኞችን በአፋጣኝ ሒደት እንደሚቀጣ ዛተ
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…