የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የየካቲት 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የአፍሪካ ህብረት በሱዳን እና በሶማሊያ የሚደረጉ የውጭ መንግስታት ጣልቃ ገብነትን አስጠነቀቀ።
    • ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር በትግራይ ክልል ሥር አድርጎ ያወጣው፣ ቦርዱ ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን "የምርጫ ክልል አደረጃጀት" በመከተሉ መሆኑን አስታወቀ።
    • በሰሜናዊ ሱዳን በአባይ (ናይል) ወንዝ ላይ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ 21 ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።
    • የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ አሽራፍ ሳሌምን አዲሱ የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።
    • በማዳጋስካር በደረሰ አውዳሚ አውሎ ነፋስ የ31 ሰዎች ሕይወት አለፈ። በ
    13 min
  • የየካቲት 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳግም ጦርነት ይጫራል ብለዉ በመሥጋት ከየቀያቸዉ የሸሹ የአለማጣ፣ የኮረምና የአካባቢዉ ነዋሪዎች የሰብአዊ ርዳታ እንዲደረግላቸዉ ጠየቁ።ከ60ሺሕ የሚበልጡት ነዋሪዎች ከየቀያቸዉ የሸሹት ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አካባቢዉን ልቅቆ በመዉጣቱ ነዉ። -የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይላት የገጠሙት ጠብ በአዲሲቱ አፍሪቃዊት ሐገር የከፋ ደም መፋሰስ ሊያስከትል እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠነቀቀ።-የኢራን እስላማዊ አብዮተኞች ሥልጣን የያዙበት 47ኛ ዓመት በጦርነት ሥጋት፣ በዛቻና ተቃዋሞ መሐል ዛሬ ተከብሮ ዋለ።
    12 min
  • የማክሰኞ የካቲት 3 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ቤኒሻንጉል፥ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ውስጥ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ማሰልጠኛ መገንባቱ ተዘገበ፤ ጄኔቫ፥ ተመድ በትግራይ ክልል ውጥረቱ እንዲረግብ ጥሪ አስተላለፈ፤ አ.አ፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግማሽ ዓመት 4.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ፤ ባሕር ዳር፥ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች ለ7ኛው አገራዊ ምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፤ ጄኔቫ፥ ተመድ ሱዳን ውስጥ ሕጻናት ለከፍተኛ ረሐብ ተጋልጠዋል ሲል አስጠነቀቀ፤ በሊቢያ የባሕር ጠረፍ በደረሰ የጀልባ አደጋ 53 ስደተኞች መሞታቸው አለያም መጥፋታቸው ተዘገበ
    11 min
  • የየካቲት 2 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ኤርትራ ከኢትዮጵያ ግዛት ሰራዊቷን እንድታስወጣና ከኢትዮጵያ አማጽያን ጋር የምታደርገውን ማንኛውም ትብብር እንድታቆም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የቀረበላትን ጥሪ ውድቅ አደረገች። ሶማሊያና ሳውዲ ዓረቢያ የጋራ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ መስማማታቸውን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳን ወደ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት (ኢጋድ) እንደምትመለስ አስታወቀች። አለፈው ሳምንት በሞስኮ በአንድ የሩስያ ጀነራል በተፈጸመው የግድያ ሙከራ የፖላንድ እጅ አለበት ሲል የሩስያ የአገር ውስጥ የስለላ መስሪያቤት አስታወቀ።
    12 min
  • የየካቲት 1ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ኤርትራ በአስቸኳይ ሰራዊቷን ከሉአላዊ ግዛቶቿ እንድታስወጣ ኢትዮጵያ አሳሰበች። • በሰሜናዊ ናይጄሪያ ካዱና ግዛት ታጣቂዎች በአንድ የኃይማኖት አባት መኖሪያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ። • ደቡብ አፍሪቃ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ልታስወጣ ነው። • አሜሪካ በትውልድ ሃገራቸው መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ በማሴር የጦር መሣሪያ ሲያዘዋውሩ ደርሼባቸዋለሁ ያለችውን ደቡብ ሱዳናዊ በእስራት ቀጣች። • በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረሱ ስምምነቶች ዋጋ አይኖራቸውም ሲሉ አንድ የእስራኤል ሚንስትር ተናገሩ ።
    8 min
  • የቅዳሜ ጥር 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና፤ በኢትዮጵያ ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል መባሉን፣የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በፈጸመው የድሮን ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ 24 ሰዎች መገደላቸውን ፣የየመን የአመራር ምክር ቤት ኃላፊ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል አዲስ ካቢኔ መሰየሙን፤ጀርመን በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ቀውሶች ወደ 1 ትሪሊዮን ዩሮ ማውጣቷን ጥናት ማመልከቱን፤ትራምፕ ኦባማን በተመለከተ የለጠፉትን የዘረኝነት ቪዲዮ ከማኅበራዊ ገፃቸው ማጥፋታቸውን እንዲሁምሩሲያ ከ400 በላይ በሆኑ ድሮኖች እና በ40 ሚሳይሎች የዩክሬንን የኃይል ማመንጫዎች መምታቷን ያስቃኛል።
    11 min
  • DW Amharic የጥር 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የበረታውን ውጥረት ለመፍታት “የሰከኑ ውይይቶች” እንደሚያስፈልጉ አሳሰበች። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በመጪው ግንቦት በሚካሔደው ሀገራዊ ምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት “የሽብር ድርጊት” ሊባል እንደሚችል የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ። በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢዝላማባድ በአንድ መስጂድ ውስጥ አጥፍቶ ጠፊ በፈጸመው ጥቃት 31 ሰዎች ሲገደሉ ከ170 በላይ ቆሰሉ።
    የሩሲያ ጦር ሠራዊት የወታደራዊ ሥለላ ምክትል ኃላፊ በሞስኮ በጥይት ተመተው ቆሰሉ።
    10 min
  • የሐሙስ ጥር 28 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አአ፥ የምርጫ ቦርድ ምርጫ የሚካሄድባቸው የፀጥታ ኹኔታ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ፤ ዋሽንግተን፥ ተመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚን የሰው ሠራሽ አስተውሎት 40 ተከታታዮች ቡድን አባል አደረገ፤ ዋሽንግተን፥ ተመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚን የሰው ሠራሽ አስተውሎት 40 ተከታታዮች ቡድን አባል አደረገ፤ ላጎስ፥የናይጄሪያ መንግሥት እስላማዊ ታጣቂዎች ላይ አዲስ ዘመቻ መክፈቱን ዐሳወቀ፤ ላጎስ፥የናይጄሪያ መንግሥት እስላማዊ ታጣቂዎች ላይ አዲስ ዘመቻ መክፈቱን ዐሳወቀ፤ ዶሃ፥ የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርትስ ከባሕረ ሠላጤው አገራት ጋር በመከላከያው ዘርፍ ትብብር፤ ካይሮ፥ ዳርፉር ረሐብ ተንሰራፍቷል ተባለ
    11 min
  • የጥር 27 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የኢትዮጵያ መንግስት በ2018 ከታቀደው ምርጫ በፊት በገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን እና በሲቪል ማህበረሰብ ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች ባወጣው አመታዊ ዘገባ አመለከተ።
    • ሶማሊላንድ በቅርቡ የሀገርነት እውቅና ከሰጠቻት እስራኤል ጋር በቅርቡ የንግድ አጋርነት ስምምነት ሃሳብ አቀረበች።
    • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ RSF በደቡባዊ ምስራቅ ይዞታዉን ኢትዮጵያን ወደ ሚያዋስኑ አካባቢዎች ማስፋቱን አስታወቀ።
    • ዕውቁ ኤርትራዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።
    11 min
  • የጥር 26 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከመንግሥታቸው ወግኖ የተዋጋው የኤርትራ ጦር በአክሱም ከተማ “ወጣቶች በጅምላ” እንደረሸነ ለመጀመሪያ ጊዜ አመኑ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባሕር ዳር ከተማ የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪም የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም ዳኜ ገዳይ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወሰነ። የሱዳን ጦር በመሐመድ ሐምዳን ደጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና አጋሮቹ በካዱግሊ ከተማ ላይ ያደረጉትን ከበባ ሰበረ። ሩሲያ ለሊቱን በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጥቃት እንደፈጸመች ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…