• ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ ጋር ከትብብር ውጭ የሚያስቡ ያሏቸውን አካላት አስጠነቀቁ ።
• የአሜሪካው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክርስቶፎር ላንዳው ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ በቀጣናው ሃገራት ጉብኝት ለማድረግ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
• የዩጋንዳ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ ፓርቲ መሪ ኪዛ ቢስጊዬ በእስር ቤት ውስጥ ተገቢው ህክምና መነፈጋቸውን ባለቤታቸው ይታወቅልኝ አሉ ።
• የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጸረ ስደተኞች ዘመቻ በበረታባት የሚኒሶታ ግዛት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የመንግስትን ዘመቻ ለመቃወም አደባባይ ወጡ።