የየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
የህወሓት ምክትል ሊ/መንበር የፌደራል መንግሥት በትግራይ ላይ ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ሲሉ ተናገሩ። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግን በትግራይ ጦርነት እንደማይከፈት አረጋግጣለሁ ብለዋል። ይሁንና ህወሓት ወታደራዊ ትንኮሳ ከገባ ግን«እንደ ቀድሞ መስሎሽ ጎርፍ ይወስድሻል» ብቻ ነው ማለት የሚቻለው» ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ከስድስት ወረዳዎች ተፈናለው በቆቦና ሰቆጣ ከተማ የሚገኙት ቁጥራቸው 100 ሺህ ይደርሳል የተባለ ሰዎች ለአንድ ወር የምግብ ድጋፍ እንዳላገኙ ተናገሩ።
አል ሞጅላድ በተባለ የሱዳን ከተማ ዛሬ የተፈጸመ የድሮን ጥቃት 18 ሰዎችን ገደለ።