የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና
    በዛሬው የዓለም ዜና፤ በሀዋሳ ከተማ በመኪና አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በአንድ ሆስፒታል ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን፤የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት አሜሪካ በሀገራቸው ላይ የጣለችው ማዕቀብ «ለሩዋንዳ ስድብ» ሲሉ መግለፃቸውን፤በኢራን ጦርነት የነዳጅ ዋጋ በማሻቀቡ የምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ማስታወቁን፤ኢራን እና እሥራኤል አንዳቸው በአንዳቸው ላይ የሚፈፅሙትን ጥቃት መቀጠሉን፤ ኢራን ዉስጥ አንድ የአሜሪካተዋጊ ጄት ተመትቶ ወደቀ መባሉን እንዲሁም ፈረንሳይ እና ደቡብ ኮሪያ የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት በጋራ እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ያስቃኛል።
    14 min
  • የመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጣሊያን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች የ19 ተሰዳጆችን አስከሬን ማግኘታቸው ተገለጸ። ሌሎች 58 ተሰዳጆችን በሕይወት አትርፈዋል።
    ከአሜሪካን የተባረሩ 12 ወደየትውልድ ሀገራቸው መመለስ የማይችሉ ስደተኞች ዩጋንዳ መግባታቸውን የዩጋንዳ የሕግ ማኅበረሰብ ዛሬ አስታወቀ።
    ኢራን በዛሬው ዕለትም በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው የአረብ ሃገራት ላይ የሚሳኤል ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች። ፕሬዝደንት ትራምፕ ኢራን ከእንግዲህ የሚያሰጋ ኃይል የላትም እያሉ ነው። ፈረንሳይ የሆርሙዝን መተላለፊያ ለማስከፈት ኃይል መጠቀሙ አዋጪ እንዳልሆነ አሳስባለች።
    ሩሲያ ቡሼር ከተሰኘው ከኢራኑ የኒኩሊየር የኃይል ተቋም ዜጎቿን ማስወጣት ጀምራለች።
    13 min
  • የመጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል "አስቻይ ኹኔታ" የለም በሚል አጀንዳ የማሰባሰብና የጉባኤ ተሳታፊ ልየታ ሥራ ዛሬ አዲስ አበባ ከሚኖሩና ከክልሉ መጡ ከተባሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር ማካሄድ በጀመረበት በዛሬው መድረክ ሥራው በክልሉ ውስጥ እንዲደረግ ተጠየቀ ።
    ሁለተኛው ወሩን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት አሜሪካና እሥራኤል የኢራን የብረታ ብረት ማምረቻዎችን ደበደቡ።
    የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሚካሄድ ምንም ዓይነት ድርድር የለም ሲሉ አስታወቁ።
    11 min
  • DW Amharic የመጋቢት 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን በገጠሙት ጦርነት ምክንያት ለኢትዮጵያ ነዳጅ የሚያቀርቡ ሀገራት በውላቸው መሠረት ማቅረብ እንደማይችሉ ማሳወቃቸውን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ተናገሩ። የሶማሊያ ጦር የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት ትልቅ ከተማ የሆነችው ባይዶዋን ተቆጣጠረ። እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራን አፀፋ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ሐገራትን ማዉደሙን ለሁለተኛ ወር እንደቀጠለ ነዉ። ጦርነቱ እንዲቆም ፓኪስታን እና ቻይና ጠይቀዋል እስራኤል በጦር ፍርድ ቤቶች ጥፋተኛ የተባሉ ፍልስጤማውያን ሁሉ በስቅላት እንዲቀጡ ያጸደቀችው ሕግ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ሥጋቱን ገለጸ።
    11 min
  • DW Amharic የመጋቢት 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የሶማሊያ ፌድራል መንግሥት እና የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ከማባባስ እንዲቆጠቡ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ አሳሰቡ። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን የሚያካሒዱት ውጊያ የሚቆምበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የቀጠናው ቁልፍ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በፓኪስታን ተሰበሰቡ። ጦርነቱ ዓለም አቀፍ ሕግ እንደሚጥስ ቡንደስታግ ተብሎ የሚጠራው የጀርመን ምክር ቤት የምርምር አገልግሎት ይፋ ያደረገው ሪፖርት አሳየ። በአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና ፖሊሲዎቻቸውን ለመቃወም በተለያዩ ከተሞች በተካሔዱ ሰልፎች ቢያንስ 8 ሚሊዮን ሰዎች ተሳትፈዋል ተብሎ እንደሚገመት አዘጋጆቹ አስታወቁ።
    9 min
  • የመጋቢት 19፣ ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ያስከተለው ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለከፋ እንግልት እያጋለጠ ነው ተባለ።
    • በዜጎች ላይ የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል ተብለው በተጠረጠሩ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት ባለቤቶች ላይ ክስ ተመሰረተ።
    • በኢራን የሚደገፉ የየመኑ ሁቲ አማፂያን በእስራኤል ላይ የሚሳይል ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቁ።
    • በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ገበሬዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ተዘገበ።
    • በሜድትራንያን ባህር ላይ በአነስተኛ የፕላስቲክ ጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 22ቱ በግሪክ የባሕር ጠረፍ መሞታቸው ተሰማ።
    10 min
  • የመጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል "አስቻይ ኹኔታ እስኪፈጠር" የክልሉን አጀንዳ የማሰባሰብ እና የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ልየታን በአዲስ አበባ ለማካሄድ መገደዱን አስታወq።። ኮሚሽኑ እንዳለው ምክክሩ ከመጋቢት 23 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
    ለአፍሪቃ ሀገራት የተላኩ የኮሌራ መከላከያ መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች በኢራን ጦርነት ምክንያት ወደሚፈለጉበት ሀገራት መድረስ አለመቻላቸው ተዘገበ። መድኃኒቶቹ ች ዱባይ በሚገኝ መጋዘን ተከማችተው እንደሚገኙተገልጿል ።
    ዛሬ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ለማለፍ የሞከሩ ሁለት እቃ ጫኝ የቻይና መርከቦች በሰርጡ ሳያልፉ ተመልሰዋል።
    11 min
  • የመጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በጅቡቲ የባሕር ጠረፍ አንድ የስደተኞች ጀልባ በመስጠሙ 9 ሲሞቱ 45ቱ እስከአሁን ደብዛቸውን ማግኘት እንዳልተቻል ፤ የኢራን እስላማዊ ዘብ የባሕር ሃይል አዛዥ በእስራኤል መገደላቸውን ተሰማ። የየመን ሁቲ አማጽያን ከኢራን ጎን እንደሚቆሙና አስፈላጊ ከሆነም በቀይባሕር ባብ አልመንደብ የሚተላለፉ መርከቦችን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ አስታወቁ። ሩስያ በደቡባዊ የኦዴሳ ግዛት በምትገኘው አንዲት የወደብ ከተማ ላይ የድሮን ጥቃት በመፈጸም በሐይል መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አደረሰች ተባለ።
    11 min
  • የረቡዕ መጋቢት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ ከምርጭ ራሳችንን እስከማግለል ርምጃ ልንወስድ እንችላለን" - የ4 ፓርቲዎች ቅንጅት፤ ካርቱም፥ የሱዳን ድንበር ከተማ ኩርሙክ አስተዳዳሪ ከተማዪቱ በፈጥኖ ደራሽ ለመያዟ ኢትዮጵያ እጇ አለበት አሉ፤ አ.አ፥ 922 ባሕር ስደተኞች በበቀይ ባሕር ያለቁበት 2025 ዓመት ከምንጊዜውም በላይ ገዳዩ ተባለ፤ ራባት፥ ሞሮኮ የአይ ኤስ አሸባሪዎች የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ከስፑን ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለጠች፤ ቴሕራን፥ ኢራን «ዩናይትድ ስቴትስ የምትደራደረው ከገዛ ራሷ ጋር ነው» አለች፤ ትሪፖሊ፥ የሊቢያ የባሕር በር ጠባቂዎች ጠባቂዎች ጉዳት የደረሰባት የሩስያ ነዳጅ ጫኝ መርከብን አሸሹ
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…