የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል የዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ጦርነት የአካባቢው አስተዳደር ሰራተኞች መታገታቸው እና ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ገለጹ። የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) አባል የአቶ ታዬ ደንደዓ አዲሱ ክስ ተቋረጠ።የኒጀር መንግሥት  2900 የሀገር ውስጥ እና የውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንቅስቃሴን አገደ።ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መርከቦች ላይ መተኮሷን ቀጥላለች።ሉፍታንዛ 20,000 የአጭር ርቀት በረራዎችን እንደሚሰርዝ አስታወቀ።
    11 min
  • የሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና የህወሐት ውሳኔ የፕሪቶሪያ ውልን ውድቅ ያደርጋል»ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለፁ፤ተቃዋሚው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግሬስ ወደ ትጥቅ ትግል መሸጋገሩን ማስታወቁን፤ናይጄሪያ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን አከሸፍኩ ማለቷን፤ በሁለተኛው ዙር የአሜሪካ-ኢራን ውይይት ቫንስ እና ቃሊባፍ እንደሚገኙ መገለጹን በ2025 8000 የሚጠጉ ሰደተኞች ጎዞ ላይ ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል ሲል የተመድ መግለፁን ፤ ኢራን ፤ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከ3,600 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች መባሉን እንዲሁምየአውሮፓ ህብረት የኃይል እጥረትን ለመፍታት የኑክሌር ማብላያዎች እንዳይዘጉ ሊያስጠነቅቅ ነው መባሉን አካቷል።
    12 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ህወሓት ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት በተካሔደ ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ወደ ሥራ እንዲመለስ” ወሰነ። ፓኪስታን ለሱዳን የጦር መሣሪያዎች እና ተዋጊ ጀቶች ለማቅረብ የገባችውን የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ሥምምነት በይደር ማቆየቷን የሀገሪቱ የደሕንነት የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። የናይጄሪያ የጸጥታ ኃይሎች በአቡጃ እና በኒጀር ግዛቶች እስላማዊ ታጣቂዎች በመንግሥት መሠረተ-ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ዐቅደዋል በሚል ሥጋት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ናቸው ተባለ። አሜሪካ የኢራንን መርከብ ከሖርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ መያዟ ዓለም አቀፍ ሕግ እና ሁለቱ ሀገሮች የተስማሙበትን የተኩስ አቁም እንደሚጥስ ኢራን አሳወቀች።
    13 min
  • የሚያዚያ11 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ለመነጋገር የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ነገ ሰኞ ፓኪስታን እንደሚገቡ መግለፃቸው፤የኢራን አጋር የሆኑት የየመን ሁቲ ሚሊሻዎች ቁልፉን የንግድ መስመር ባብ ኤል ማንዳብን እንደሚዘጉ በድጋሚ ማስጠንቀቁ፤ሶሪያ በሂዝቦላህ እና በቀድሞው መሪ አሳድ ቅሪቶች ሊፈፀም ነበር ያለችውን ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት ማክሸፏን መግለጿ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና ሃንጋሪ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለመልቀቅ የሚያስችል 'ቴክኒካዊ' ውይይት ማድረጋቸው መግለፃቸውን አካቷል።
    7 min
  • የሚያዝያ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ስምንት ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሰባሰበው "ሠላም ለኢትዮጵያ" የተባለው ጥምረት፣ በጥምረቱ ላይ ደረሱ ያላቸው ጥሰቶችና ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ራሱን ከምርጫ ለማግለል እንደሚገደድ ገለፀ። አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷን የምትቀጥል ከሆነ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን መልሳ እንደምትዘጋ ዛሬ አስጠነቀቀች። እስራኤል የደህንነት ስጋትን ተጨማሪ ቦታ ለማስፋፋት እየተጠቀመችበት ነው ሲሉ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሰሱ።
    13 min
  • የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ኮሬ፥ ደቡብ ኢትዮጵያ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ከፍተው ነዋሪዎችን ገደሉ፤ ኪንሻሳ፥ ከዩናይትድ ስቴትስ በግዳጅ የተሰናበቱ 15 ደቡብ አሜሪካውያን ኮንጎ ደረሱ፤ ቤሩት፥ እሥራኤል እና የሊባኖሱ ሒዝቦላህ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ፤ ዋሽንግተን፥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍኖተ-ሆርሙዝ ከእንግዲህ «መቼም» አይዘጋም አሉ፤ ቴሕራን፥ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ተኩስ አቁሙ ተጥሶ ጥቃት ቢደርስበት እንደሚበቀል አስጠነቀቀ፤ ናይፒይዳው፥ ምያንማር በዓመታዊ ልማዷ 4,000 እስረኞችን ነጻ ለቀቀች
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም
    ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ እና ሲቪል የለበሱ በተባሉ ሰዎች ከሥራ ቦታው የተወሰደው የአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር ሚሊዮን በየነ እስካሁን ያለበት ቦታ እንዳልታወቀ ተገለፀ። -ትራምፕ «እስራኤል እና ሊባኖስ ለ10 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል»-የኬንያ ፍርድ ቤት አንድ ቻይናዊ ህገ-ወጥ የጉንዳን አዘዋዋሪ ላይ የአንድ ዓመት እስራት ፈረደ።-የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በካሜሩን የሚገኙ ባለስልጣናት ሕሊናቸውን እንዲመረምሩ እና "የሙስና ሰንሰለትን" እንዲሰብሩ ጥሪ አቀረቡ።
    10 min
  • የሚያዝያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አራተኛ ዓመቱን በያዘው የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት በረሐብ እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖችን ለመርዳት ጀርመን 20 ሚልዩን ዩሮ እንደምትለግስ አስታወቀች። አሜሪካ ከኢራን ወደቦች የሚወጡና የሚገቡ መርከቦችን ማገዷን ከቀጠለች በቀይባሕር፣ የፐርሺያ ባሕረሰላጤና በኦማን የባሕር ሰርጥ የሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ እንደምታግድ ኢራን አስጠነቀቀች። እስራኤል በአለፉት 24 ሰዓታት በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ ከ200 በላይ «የሒዝቦላሕ ወታደራዊ ይዞታዎች» ባለቻቸው ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች።
    11 min
  • የሚያዚያ 6 ቀን 2018 ፤የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና ፤የናይጄሪያ ፖሊስ በምዕመናን እገታ የተሳተፉ 33 አባላት ያሉት የወሮበሎች ቡድንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለፁ፤የቤኔን የምርጫ ኮሚሽን የዘንድሮውን ሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ይፋ ማድረጉን፤ሊባኖስ እና እስራኤል ቀጥተኛ የዲፕሎማሲ ውይይት ዛሬ በዋሽንግተን ማካሄዳቸውን፣በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ የዓለም አቀፍ የእድገት ትንበያ መቀነሱን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መግለፁን፤ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ ንግግራቸውን ዳግም እንዲቀጥሉ ፈረንሣይ ጥሪ ማቅረቧን እንዲሁም የጀርመን መራሄ መንግስት አውሮጳ በማንኛውም የዩክሬን የሰላም ስምምነት ውስጥ መሳተፍ እንዳለባት ማለታቸውን ያስቃኛል።
    12 min
  • የሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሱዳናውያን ሕይወታቸውን ለመታደግ ሲሉ ቅጠላ ቅጠልና የእንስሳት መኖ ጭምር ለመመገብ መገደዳቸውን 5 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስታወቁ። በናይጄርያ ሰሜን ምስራቅ በምትገኝ አንዲት መንደር የሐገሪቱ አየር ሃይል በገበያ ቦታ ፈጸመው በተባለው የአየር ድብደባ ቢያንስ 200 ሰላማዊ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰግቷል። የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ወደቦች በሙሉ እንዲዘጉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ኢራን ፈጣን የዛቻ ምላሽ ሰጥታለች።
    13 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…