የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የኦሮሞ ነፃነት ጦር አባላት በአዳጊና አዋቂ ሴቶች ላይ የፈጸሟቸውን አስገድዶ መድፈር፣ የቡድን ወሲባዊ ጥቃት፣ የወሲብ ባርነት፣ አሰቃቂ ግድያና ጾታዊ ጥቃቶችን መርምረው አጥፊዎች እንዲጠየቁ እንዲደርጉ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ።
የተመድ ዩጋንዳ ሲቪሎች የተገደሉበትና ክፉኛ የተቃጠሉበትን የደቡብ ሱዳንን የአየር ጥቃት አግዛለች የሚል መረጃ ይፋ አደረገ።
በመካከለኛው ምሥራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት ሰባተኛ ቀን የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ቴህራንና ቤይሩትን መደበብደባቸው እየተዘገበ ነው።
በፓኪስታንና አፍጋኒስታን ግጭት 56 ሲቪል የአፍጋን ዜጎች መገደላቸውን ከመቶ በላይም መጎዳታቸው የተመድ አስታወቀ።