አርስተ ዜና
-የዩክሬን ፕሬዚዳንት የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ የአገራቸው ምርጥ የደህንነት ዋስትና ነው ሲሉ ተናገሩ። ዜሌንስኪ ዩናይትድ ስቴትስ ግን ይህን ለመቀላቀል እና ለዩክሬን ለመቆም "ዝግጁ አይደለችም" ብለዋል።
-የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነትን እየጣሰ ነው ሲል ህወሓት ከሰሰ። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት በመግለጫዉ የጊዚያዊ አስተዳደርን በተመለከተ “የተናጠል” ውሳኔ ማስተላለፍ አይቻልም ሲል ትላንት ጠ/ሚ አብይ ለትግራይ ህዝብ ያስተላለፉትን የፕሬዚደንት ጥቆማ ጥሪ ተችቷል።