የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
-ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉ ይበልጥ እንዳሰጋቸው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ ተናገሩ።
-የናፍጣ እጥረት ባናረው የጭነት መጓጋዣ ዋጋ ምክንያት፣ የሙዝ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቸገራቸውንና ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑንም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ሙዝ አምራች አርሶ አደሮች ዐሳወቁ።
-ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ የኢራኑን ጦርነት ለማስቆም ያቀረበችውን የሰላም እቅድ እየገመገመች መሆኑን ኢራን አሳወቀች።