የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ማክሰኞ
    -አርሰተ ዜናዎች--ሩሲያ በዩክሬን ላይ በድጋሚ በሰነዘረችዉ ከፍተኛ ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገደሉ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ።-በኢትዮጵያ የተካሄደው የሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምፅ ቆጠራ ውጤት፣ በምርጫ ጣቢያዎች እየተለጠፈ ይገኛል።--በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ሀገረ ስብከት በአስኮ ወረዳ በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች መገደላቸውን ሀገር ስብከቱ አመለከተ። የመቶ አንድ ዓመት እድሜ እንደነበረው የተገለጸው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንም ሙሉ በሙሉ በእሳት መጋየቱ ተነግሯል።
    12 min
  • DW Amharic የግንቦት 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የጋምቤላ ክልል ፖሊስ “የተለየ የይለፍ ፈቃድ ካልተሰጠ በቀር” ማንኛውም ተሽከርካሪ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት መንቀሳቀስ እንደማይችል አስታወቀ። በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አምስት ሕሙማን ከኢቦላ ማገገማቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኃኖም ተናገሩ። ኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ድርድር የኑክሌር የጦር መሣሪያ ላለመስራት መስማማቷን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ። የኢራን ዋና ተደራዳሪ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ ግን “የኢራናውያን መብቶች መከበራቸውን ሳናረጋግጥ አንዳች ሥምምነት አናጸድቅም” ብለዋል።
    9 min
  • የግንቦት 22 ቀን 2018 ፤የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና፤የአማራ ፋኖ የጣለው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ የምርጫ ሥራዉን ስለማስተጎጎሉ የደረሰው መረጃ እንደሌለ ምርጫ ቤርድ ማስታወቁ፣የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የኢቦላ ወረርሽን ወደተቀሰቀሰባት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ማምራታቸውን፣ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ መስጠቷን፣ በጀርመን የሙኒክ አውሮፕላን ማረፊያ አጠራጣሪ ድሮን መታየቱን ተከትሎ ለአጭር ጊዜ በረራ መቋረጡን አሜሪካ ስምምነት ላይ ካልደረሰ በኢራን ጦርነቱን እንደገና ለመጀመር ዝግጁ መሆኗን መግለጿን፣እንዲሁምሩሲያ፤ በአርሜኒያ የሚገኙ አምሳደሯን መጥራቷን አካቷል።
    10 min
  • የግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ከአማራ ክልል መንገደኞችን ጭኖ ትናንት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ አውቶብስ ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ።
    ማዕከላዊ ኬንያ ውስጥ በሚገኘው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት የተነሳውን እሳት በመለኮስ የተጠረጠሩ ስምንት ተማሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
    የኬንያ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በኤቦላ ተሐዋሲ ለተያዙ የአሜሪካ ዜጎች አግልሎ ማቆያ የማዘጋጀት እቅድን በጊዜያዊነት አገደ።
    ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለገባችበት ውዝግብ ለታሰበው የሰላም ስምምነት ከቃል ይልቅ ተግባር እንደምትፈልግ አስታወቀች።
    12 min
  • DW Amharic የግንቦት 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በጥሞና ወቅት “ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ” ከለከለ። ክልከላው የምርጫውን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ያግዛል በተባለው የጥሞና ጊዜ ከማይደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተካተተ ነው። ከኢትዮጵያ መንግሥት የሚዋጋው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ በአማራ ክልል “ለተከታታይ አምስት ቀናት ከአንቡላንሶች በስተቀር ሁሉም መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ መደረጋቸውን” አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት አገሪቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር የተበደረችበት ቦንድ ባለቤቶችን ከሚወክል ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር ያደረገው ውይይት ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
    11 min
  • የረቡዕ ግንቦት 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ ለቀጣዩ ምርጫ ሥራ ዝግ እንደሚኾን ምርጫ ቦርድ ዐሳወቀ፤ አ.አ፥ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላ ኢትዮጵያ ተከበረ፤ ጆሐንስበርግ፥ የጋና መንግሥት ዜጎቹን መጤ ጠል ሥጋት ካጠላባት ደቡብ አፍሪቃ ወደ አገራቸው እየመለሰ ነው፤ ዋሽንግተን፥ ካናዳ እና ባሐማ ከኤቦላ ጋር የተገናኘ የጉዞ ክልከላ ተግባራዊ አደረጉ፤ ናይሮቢ፥ ካናዳ እና ባሐማ ከኤቦላ ጋር የተገናኘ የጉዞ ክልከላ ተግባራዊ አደረጉ፤ ጋዛ፥እሥራኤል አዲስ የተሾሙ የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥን መግደሏን ዐሳወቀች፤
    10 min
  • የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና
    የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በሱዳኑ ጦርነት ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል በምህጻሩ RSF ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ ኮሎምብያውያን የግል ቅጥረኛ ወታደሮችን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ታሰለጥናለች ሲል ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ።
    በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እጎ ዩጋንዳ ዉስጥ ተጨማሪ ሰዎች በኢቦላ ተሕዋሲ መያዛቸዉን የሁለቱ ሐገራት የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ።
    ኢራን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት የፈጸመችባትን የአየር ድብደባ አወገዘች። ድብደባዎቹን የተኩስ አቁሙን የጣሰ ሲል ያወገዘው የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ ጥቃቶቹ ለሚያስከትሉት መዘዞች ሁሉ ዋሽንግተን ሃላፊነቱን እንደምትወስድ አስጠንቅቋል።
    11 min
  • የግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    መገናኛ ብዙኃን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመንግሥት ቁጥጥር ስር በሆነበት፤ አመጽና ዛቻን በመጋፈጥ፤ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ እንደሚሳተፉ ተዘገበ።
    ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልእኮ የወታደሮች ቁጥር በመቀሱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንድ ጥናት አመለከቱ።
    ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነቱን ለማስቆም ከአሜሪካ ጋር የምታካሄደው ድርድር መሻሻሎች ቢኖሩትም ስምምነት ላይ ገና አልተደረሰም አለች። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከኢራን ጋር የሚደረገው ስምምነት ወይ ታላቅና ትርጉም ያለው ይሆናል ወይ ደግሞ ስምምነት አይኖርም ብለዋል።
    11 min
  • የግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ የሟቾች ቁጥር 204 ደረሰ። ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 የአፍሪካ ሀገራት ወረርሽኙ አስግቷቸዋል።
    • አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸው ተሰማ።
    • ሩሲያ ዛሬ ሌሊት በዩክሬን መጠነ-ሰፊ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት “ኦሬሽኒክ” የተሰኘውን የሃይፐርሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳኤል
    • በፓኪስታን በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት የ23 ሰዎች ህይወት አለፈ።
    • ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ ኬፕታውን ውስጥ የተደረገውን የማራቶን ሩጫ የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፉ ።
    8 min
  • የግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኡጋንዳ በተጨማሪ 10 የአፍሪካ ሐገራት የኢቦላ ቫይረስ ሥርጭት እንደሚያሰጋቸው የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት አስታወቀ። ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ ዳግም ጦርነት የምታውጅ ከሆነ ብርቱ አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ ኢራን አስጠነቀቀች። በሰሜን ቻይና በምትገኝ የሻንዚ ግዛት በአንድ የከሰል ማዕድን ማውጫ ትላንት ባጋጠመ ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 90 መድረሱን ተሰማ። ዩክሬይን በሩስያ ቁጥጥር ሥር በሚገኘው እና የቀድሞ ግዛቷ በነበረው ሉጋንስክ ከተማ ፈጸመችው በተባለ የድሮን ጥቃት 18 ሰላማዊ ሰዎች ሲሞቱ 48 መቁሰላቸውን የአካባቢው የሩስያ ገዢ አስታወቁ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…