የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሬ ዞን ተማሪዎች እስካሁን የዓመቱን የማጠቃለያ ፈተና እንዳልተፈተኑ ወላጆች ገለጹ። መምህራኑ «መንግሥት የኑሮ ውድነትን ለመደጎም ያደረገው ውዝፍ የደመወዝ ጭማሪ በተሟላ ሁኔታ አልተከፈለንም» በሚል ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም ተብሏል።
    በሰሜናዊ ናይጀሪያ ማለቂያ ባጣው ግጭት ምክንያት ታይቶ የማይታወቅ ረሀብ መከሰቱን ዛሬ የተመድ አስታወቀ።
    የኬንያ ፍርድ ቤት በስምንት ተማሪዎች ላይ የግድያ ክስ መሰረተ።
    ዛሬ ማለዳ ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 21 ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አመለከቱ። 86 ሰዎችም ተጎድተዋል።
    12 min
  • የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. አርእስተ ዜና
    አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ RSFን በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎችና በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ ።
    ትውልደ-ኢትዮጵያዊቷ ሶሻል ዴሞክራት ሜላት ኪሮስ ትናንት ማክሰኞ በአሜሪካ በዴንቨር አካባቢ የተካሄደውን ምርጫ አሸነፉ። ሜላት ኪሮስ ለ15 ጊዜ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትን ዲያና ደጌትን ነew ያሸነፉት
    ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በቀጠር ዋና ከተማ ዶሀ ዛሬ ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል ።
    10 min
  • የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የተመድ የኢቦላ ወረርሽኝ አፍሪቃን እስከ 3,6 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ያስወጣታል አለ።
    የኬንያ ፖሊስ በዛሬው ዕለት እገታን በመቃወም አደባባይ የወጡ ናቸው በተባሉ ሰዎች ላይ ጥይት ተኩሶ አንድ ሰው መግለደሉን እማኞች አመለከቱ። ሁለት ሰዎችም በጥይት ተጎድተዋል።
    የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በሱዳን አል ኦቢድ ጉዳይ አስቸኳይ ክርክር ሊያካሂድ መሆኑ ተገለጸ። በተጠቀሰችው ከተማ ዙሪያ የፈጥኖ ደራሹና ደጋፊዎቹ ኃይሎች መከማቸታቸው ስጋት አስከትሏል።
    ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመጪዎቹ ቀናት የመገናኘት እቅድ የለኝም አለች። ሁለት የአሜሪካ ልዑካን በኢራን ጉዳይ ለመነጋገር ዛሬ ቀጠር መግባታቸው ተዘግቧል።
    12 min
  • DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ማሕሙድ ተገናኙ። ለ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ቅንጡ የእጅ ሰዓቶችና ማዳመጫዎች ወደ መፈተኛ ክፍል ይዘው መግባት ተከለከሉ። ኢትዮጵያ አንድ ቢሊዮን ዶላር የተበደረችበት ቦንድ ባለቤቶችን ከሚወክል ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ ለማድረግ በመርኅ ደረጃ ከሥምምነት መደረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኬንያ መንግሥት ከአሜሪካ ጋር ሊፈራረም ነው የተባለው የውድ ማዕድናት ፍለጋ “ግልጽነት ይጎድለዋል” የሚል ክስ በፍርድ ቤት ቀረበበት። በጀርመን ኒደር ዛክሰን ግዛት ሽታደ ከተማ በተከፈተ ተኩስ 5 ሰዎች ተገደሉ
    10 min
  • የዕሁድ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ. ም ፤ የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና በሳውዲ አረቢያ እና በፈረንሳይ በደረሰ የሄሊኮፕተር እና የአውሮፕላን አደጋ 25 ሰዎች መሞታቸውን፣ በአውሮጳ በተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ1,300 በላይ ሞት መመዝገቡን፣ ቢያንስ 191 ሚሊዮን ሰዎች ለ35 ዲግሪ ሴልሺየስ ሙቀት ይጋለጣሉ መባሉን፣ ኢራን የአሜሪካን ጥቃት ተከትሎ በባህሬን እና ኩዌት ላይ ጥቃት ማድረሷን እንዲሁም የዩክሬንን ጥቃት ተከትሎ የሩሲያው መሪ የሀገራቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ቃል መግባታቸውን አካቷል።
    9 min
  • የሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮጳ ኅብረት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እያካሔደ ነው የተባለው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ የፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ስምምነት በግልጽ የጣሰ ነው ሲል ነቀፈ።
    • በሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ የሚካሄደው ውጊያ ወደ ከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠነቀቀ።
    • የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት በጎረቤት ሩዋንዳ ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት (ICJ) ክስ መሰረተች።
    • ኢራን አሜሪካን "ጦርነቱን ለማቆም የተደረገውን ስምምነት ጥሳለች" ስትል ከሰሰች።
    12 min
  • የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቐለ፥ ሕወሓት ለሒውማን ራይትስ ዎች ምላሽ ሰጠ፤ ካርቱም፥ በሱዳን ኤል ኦቤይድ ከተማ ላይ ሌላ ፍጅት እንዳይከሰት አሥግቷል፤ ቱኒስ፥ ኃዋቂዋ ቱኒዚያዊት የ75 ዓመት የመብት ተሟጋች 25 ዓመት እስር ተፈረደባቸው፤ ዋሽንግተን፥ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሔይቲ እና ሶሪያ ዜጎች በገፍ ከአገር እንዲባረሩ የሚያስችል መንገድ ጠረገ፤ ፓሪስ፥ አውሮጳን የመታው የሙቀት ማእበል እንደበረታ ነው፤ ካራካስ፥ ከብርቱው ርእደ መሬት የተረፉትን ለማዳን ርብርቡ ቀጥሏል፤ ኒው ጄርዚ፥ የዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ እየተገባደደ ነው
    11 min
  • የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኬንያ ፖሊስ በዛሬው ዕለት ናይሮቢ በሚገኘው ዋና የፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ የተሰበሰቡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ በተነ።
    ቬንዝዌላን ባናወጠው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ የ164 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን 971 ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አስታወቁ። በርካታ ሃገራት ለእርዳታ እጃቸውን ዘርግተዋል።
    የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ እስራኤል ከመላ ሊባኖስ መውጣት እንደሚኖርባት አመለከቱ። እስራኤል ሂዝቦላህ ትጥቁን ሳይፈታ ኃይሌን አላወጣም ብላለች።
    ፈረንሳይ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያለው ነዳጅ ጫኝ መርከብን በሲሲሊ የባሕር ዳርቻ ላይ መያዟን አስታወቀች። ሩሲያ ድርጊቱን አውግዛ የባሕር ላይ ውንብድና ብላዋለች።
    13 min
  • የሰኔ 17 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ራሱን የሊቢያ «የመረጋጋት መንግሥት» ብሎ የሚጠራዉ የምሥራቅ ሊቢያ ስብስብ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ፣ የኤርትራና የሱዳን ዜጎች ሊቢያ እንዳይገቡ አገደ።---አዉሮጳን የገለበዉ የሙቀት ማዕበል የሰዎች ሕይወት እያጠፋ፣የትምሕርት ሒደት፣ሥራና እንቅስቃሴንም እያስተጓጎለ ነዉ።አለቅጥ የናረዉ ሙቀት ያንገበገባቸዉ አንዳድ ሰዎች ዘለዉ ወንዝ፣ኩሬና ገንዳ ዉስጥ እየገቡ ሞተዋል።--የዓለም የአዉቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅት (IAEA) የኢራንን የኑክሌር ተቋማትና ንጥረ ነገር በቅርቡ እንደሚፈትሽ አስታወቀ።ኢራን ግን የኑክሌር ጉዳይ የሚነሳዉ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያደረገችዉ ሥምምነት ገቢራዊነት ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ ትላለች።
    12 min
  • የሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ ም የዓለም ዜና
    ግብፅ ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ጋር በተያያዘ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋለች።ዩጋንዳ ውስጥ አንድ አዲስ ሰው ላይ ኤቦላ ተረጋገጠ፤ በጠቅላላው 20 ሰዎች ተይዘዋል
    እስራኤል ወደፊት የጦር መሣሪያ አቅርቦትን በተመለከተ የዩናይትድ ስቴትስ ጥገኛ መሆን እንደማትፈልግ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ አስታወቁ።
    አምስት ልዑካንን ያቀፈ የታሊባን ቡድን ዛሬ ከአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ለመምከር ብራስልስ ገባ።
    ዶይቸ ቬለ DW በየዓመቱ የሚያካሂደው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ዛሬ ማክሰኞ በቦን ከተማ መካሄድ ጀመረ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…