የዓለም ዜና

የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና


Listen Later

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ አውቶብስ ላይ ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ስድስት ሰዎችም ተጎድተዋል። ጥቃት አድራሾቹ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች መሆናቸው ተገልጿል።
የግሪክ ባሕር ኃይል ከ500 በላይ ስደተኞችን ከመስመጥ ማዳኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ።
ዩጋንዳ ከጀርመን ጋር መከላከያን በተመለከተ ያላትን ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች።
የእስራኤል መንግሥት በቅርቡ ጋዛ ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነገረ። ሃገራት እስራኤል ጋዛ ላይ የምትወስደውን የኃይል እርምጃ እንድታቆም እየጠየቁ ነው።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW