Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት... more
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 475 episodes available.
June 24, 2025የዓለም ዜና፤ ሰኔ 17 ቀን፣ 2017 ማክሰኞ--ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሰዋል ሲሉ ወቀሱ። በሌላ በኩል ኢራን የኒኩሊየር ተቋሞችዋን ለማደስ ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆንዋን አስታዉቃለች።--የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት የ(ኔቶ) መሪዎች ኔዘርላንድስ ላይ ታሪካዊ የተባለዉን የሁለት ቀናት ጉባኤ ጀመሩ። 32 የዓለም ሃገራት አባላት የሆኑበት የዓለም ትልቁ የደህንነት ድርጅት ለደህንነት ተጨማሪ ወጭ ለማዉጣት ይስማማሉ አልያም ያለስምምነት ይበተናሉ ተብሎ ይጠበቃል።--በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡኔ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም በሚኖሩ መነኮሳት ላይ በተፈጸመ ጥቃት የአንድ መናኝ ህይወት ጠፋ፤ አንድ አባት ጉዳት ደርሰባቸዉ።...more14minPlay
June 23, 2025የሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜናኢራን ትናንት እሑድ በአሜሪካ ለደረሰባት ጥቃት አጸፋዋ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ዛተች። አሜሪካ ኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ የኢራን እስራኤል ፍጥጫ በዲፕሎማሲ መፍትሄ እንዲያገኝ የተለያዩ ሃገራት ጥሪ አቀረቡ። ቴህራን በበኩሏ በዩናይትድ ስቴትስ የተፈጸመባት ጥቃት የዲፕሎማሲ እና ውይይት መርሆዎችን መካድ ነው ብላለች። የሶማሊያ ጦር ኃይላት በትናንትናው ዕለት በሀገሪቱ ማዕከላዊ አካባቢዎች ቢያንስ 20 የሚሆኑ የአሸባብ ተዋጊዎችን ገደሉ። በርካቶችንም አቆሰሉ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ቡድናቸው ከግብጽ ጋር ያለውን ያለመግባባት በውይይት ለመፍታት እንደሚፈልግ አስታወቁ።...more12minPlay
June 21, 2025የሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜናበናይጄሪያ አንዲት ሴት አጥፍቶ ጠፊ በፈጸመችው የቦምብ ጥቃት 20 የጸረ እስላማዊ ጀሃድ ታጣቂዎች መገደላቸውን ተሰማ።እስራኤል ኢስፋሃን የሚገኘውን የኢራን የኒኩሌር ማብለያ ተቋም ላይ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። እስራኤል በተቋሙ ጥቃት ብትፈፅምም ምንም አይነት ሰዎችን ሊጎዳ የሚችል ኬሚካል አለመፍሰሱን አክለዋል። የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ኢራን የኒኩሌር የጦር መሳሪያ ስለማምረቷ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃ እንደሌለ ለእስራኤል ደጋግመን ነግረናታል አሉ።...more11minPlay
June 20, 2025የሰኔ 13 ቀን 2017 የዓለም ዜና-የኢጣሊያና የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች የአፍሪቃ ሥደተኞችን ለመግታት ለተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት ሊሰጥ ሥለታቀደዉ ርዳታ ዛሬ ተነጋገሩ።---የሥደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ የአዉሮጳ ሕብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ14 የአፍሪቃ ሐገራት 5.5 ቢሊዮን ዩሮ ይሰጣል።---የእስራኤልና የኢራን የጦር ሜዳ ዉጊያ የዲፕሎማሲ እንኪያ ሰላንቲያም ዛሬም እንደመሰንበቻዉ ቀጥሎ ዉሏል።የእስራኤል ጦር የኢራን የሚሳዬል ማወንጨፊያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን መደብደቡን አስታዉቋል።የኢራን ሚሳዬሎችም ዛሬ በእስራኤል ግዛቶች ላይ ሲዝንቡ ነዉ የዋሉት።-በዲፕሎማሲዉ መስክ የኢራንና የሶስት የአዉሮጳ ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች እየተነጋገሩ ነዉ።...more12minPlay
June 19, 2025የሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና*በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን 17 ንጹሀን ዜጎች በታጣቂዎች ተገደሉ*ፍርድ ቤት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባን በነጻ አሰናበተ*ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ የሰላም ስምምነት ሊፈራረሙ ነው*እስራኤል በኢራን ላይ የአፀፋ ርምጃ እንደምትወስድ አሳሰበች*ዜጎችን ከእስራኤል እና ኢራን የማስወጣት ርምጃው ቀጥሏል*ሩሲያ ጀርመንን አስጠነቀቀች...more11minPlay
June 18, 2025የሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜናበአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መንግሥት ወደየቀያቸው እንዲመልሳቸው ጠየቁ። የትራምፕ አስተዳደር ዜጎቻቸው ላይ የጉዞ እገዳ እንዳይጣል ተገቢውን ማጣሪያ እንዲያደርጉ ለ36 ሃገራት ማሳሰቢያ ሰጠ። ማሳሰቢያው ከደረሳቸው 25ቱ የአፍሪቃ ሃገራት ሲሆኑ ኢትዮጵያ አንዷ ናት።እስራኤል ሁለት የኢራን የኒኩሊየር ማብላያ የሚገኝባቸው ሕንጻዎች አወደመች። ኢራን በአሜሪካ ድጋፍ ተደርጓል ላለችው ጥቃት የምትመልሰው አጸፋ የከፋ እንዲሚሆን ዝታለች። እስራኤል ለጥቃቱ ከ50 በላይ ተዋጊ ጀቶችን ማሰለፏን አስታውቃለች ።...more12minPlay
June 17, 2025የዓለም ዜና፤ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞአርስተ ዜና፤ --ኤርትራዉያን ስልታዊ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸዉ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት አጋለጠ። --በእስራኤል የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በሀገሪቱ የሚገኙ የቻይና ዜጎች በሙሉ እስራኤልን በድንበር በኩል አቋርጠው እንዲወጡ አሳሰበ። በሌላ በኩል እስራኤል በኢራን ላይ የምታካሂደዉ ጥቃት በመቀጠሉ ጋና ዜጎቿን ከኢራን ማስወጣት ጀመረች።--ቡድን ሰባት በመባል የሚታወቁት ሰባቱ የበለፀጉት ሀገራት መሪዎች ትናንት ካናዳ ላይ የጀመሩትን ጉባኤ ዛሬ ለሁለተኛ ቀን እንደቀጠሉ ነዉ።--ፕሬዚዳንት ትራምፕ በበኩላቸዉ በመካከለኛዉ ምስራቅ ቀዉስን ተከትሎ አቋርጠዉ ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል።...more13minPlay
June 16, 2025የሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜናኢራንና እስራኤል ዛሬም ለአራተኛ ቀን አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚሳይል ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ቀጥለዋል። ኢራን ዛሬም ወደተለያዩ የእስራኤል ከተሞች ባስወነጨፈቻቸው ሚሳይሎች በደረሱ ጥቃቶች 11 ሰዎች ተገድለዋል። የተ።መ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ግፊት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ ሁሉም ከተኛበት ነቅቶ ግጭቱን ለማስቆም በእስራኤልና በሀማስ ላይ ግፊቱን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።ቡድን ሰባት የሚባለው የዓለም ባለፀጋ ሀገራት ስብስብ የመሪዎች ጉባኤ በካናዳዋ በካናናስኪስ ከተማ ውስጥ ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይጀምሯል።...more11minPlay
June 15, 2025DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2017 የዓለም ዜናበዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ 36 ሀገራትን የጉዞ ዕቀባ ከጣለባቸው ጎራ የማካተት ዕቅድ አለው ተባለ። በጋዛ ሠርጥ በእስራኤል እና በአሜሪካ ድጋፍ ምግብ በሚታደልበት ቦታ በተከፈተ ተኩስ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌላቸው ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጨመረ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በቡድን ሰባት ሀገራት ስብሰባ ላይ የእስራኤል እና የኢራንን ግጭት ለማቆም በአራት ጉዳዮች ላይ ከሥምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ። በሰሜናዊ ሕንድ ሔሊኮፕተር ተከስክሶ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ።...more9minPlay
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 475 episodes available.