ኢራንና እስራኤል ዛሬም ለአራተኛ ቀን አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚሳይል ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ቀጥለዋል። ኢራን ዛሬም ወደተለያዩ የእስራኤል ከተሞች ባስወነጨፈቻቸው ሚሳይሎች በደረሱ ጥቃቶች 11 ሰዎች ተገድለዋል።
የተ።መ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ግፊት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ ሁሉም ከተኛበት ነቅቶ ግጭቱን ለማስቆም በእስራኤልና በሀማስ ላይ ግፊቱን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
ቡድን ሰባት የሚባለው የዓለም ባለፀጋ ሀገራት ስብስብ የመሪዎች ጉባኤ በካናዳዋ በካናናስኪስ ከተማ ውስጥ ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይጀምሯል።