በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መንግሥት ወደየቀያቸው እንዲመልሳቸው ጠየቁ።
የትራምፕ አስተዳደር ዜጎቻቸው ላይ የጉዞ እገዳ እንዳይጣል ተገቢውን ማጣሪያ እንዲያደርጉ ለ36 ሃገራት ማሳሰቢያ ሰጠ። ማሳሰቢያው ከደረሳቸው 25ቱ የአፍሪቃ ሃገራት ሲሆኑ ኢትዮጵያ አንዷ ናት።
እስራኤል ሁለት የኢራን የኒኩሊየር ማብላያ የሚገኝባቸው ሕንጻዎች አወደመች። ኢራን በአሜሪካ ድጋፍ ተደርጓል ላለችው ጥቃት የምትመልሰው አጸፋ የከፋ እንዲሚሆን ዝታለች። እስራኤል ለጥቃቱ ከ50 በላይ ተዋጊ ጀቶችን ማሰለፏን አስታውቃለች ።