አርዕሥተ ዜና
-የኢድ አል አድሐ በዓል ዛሬ በአብዛኛዉ ዓለም በሙሊሞች ዘንድ መከበር ጀመረ።ከሱዳን እስከ ምያንማር፣ ከጋዛ እስከ ካሽሚር የሚደረጉ ጦርነት፣ ግጭትና የመብት ረገጣዎች የመንፈሳዊዉን በዓል ድባብ አጥልተዉበታል።የሐጂ ሥርዓት ግን እስከ ዛሬ ብዙ መጨናነቅና አደጋ አልታየበትም ተብሏል።
-የሩሲያ ጦር በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፈተ።የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮልድሚየር ዘለንስኪ እንዳሉት አብዛኞቹ የየኩሬን ከተሞች «አረመኒያዊ» ባሉት ጥቃት ክፉኛ ተደብድበዋል።-ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ዳኞች ላይ ማዕቀብ መጣልዋን ፍርድ ቤቱ አወገዘ። ድርጅቶች አጥብቀዉ ተቃወሙት።