-መቀሌ ዉስጥ ዛሬ አደባባይ የተሰለፉ የትግራይ ተፈናቃዮች የክልሉ ፕሬዝደንት ፅሕፈት ቤት የሚገኝበትን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ ገቡ።ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደቀያቸዉ እንዲመለሱ በተደጋጋሚ በአደባባይ ሠልፍ እየጠየቁ ነዉ።---የኢትዮጵያ መንግስት የሕግ ሒደትንም ሆነ የፕሬስ ነፃነትን እንደማያከብር ሁለት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታወቁ።--ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ካጠቃች የኢራን ጦር መካከለኛዉ ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮችን እንደሚመታ የኢራን መከላከያ ሚንስትር አስጠነቀቁ።