በኢትዮጵያ “ኤምፖክስ” ተብሎ በሚጠራው የጦጣ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ መንግሥት እና ሕዝብ ለኢትዮጵያ “ተሐድሶ ወይም ለውጥ በከፍተኛ ተስፋ ባደረጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ ድንገት በተፈጠሩ ክስተቶች ምክንያት እንደማይቆጩ” ተናገሩ። በጋዛ በአንድ ቀን 38 ሰዎች በእስራኤል ጥቃቶች መገደላቸውን የሐማስ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሩሲያ እና ዩክሬን በሦስት ዙር ያካሔዱትን የጦር ምርኮኞች ልውውጥ አጠናቀቁ። የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዶብሪንት የተወሰኑ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን ወደ ጀርመን ከማምጣት የሚከለክል ሕግ እየተዘጋጀ መሆኑን አረጋገጡ።