የዓለም ዜና

DW Amharic የግንቦት 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና


Listen Later

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች “ጦርነት ይቁም፣ ግፋዊ አገዛዝ ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ” የሚል ጥሪ ያቀረቡበትን ትዕይንተ-ሕዝብ በበይነ-መረብ አካሔዱ። በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “በፖለቲካዊ እና የብሔር ልዩነት ምክንያት የተቀሰቀሰ የትጥቅ ግጭት እየተባባሰ” መሔዱን የአውሮፓ የሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ ርዳታ ሥራ ክፍል አስታወቀ። በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በጎርፍ 1,753 አባወራዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ ነዋሪዎች መንደራቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ። በዩክሬን ኻርካይቭ ላይ ሩሲያ በድሮኖች እና ሚሳይሎች በፈጸመችው ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW