የጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
የኦሮሚያ ክልል የሰላሌ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በግጭቱ ምክንያት ሕይወታቸው ለአደጋ መጋለጡን ለዶቼቬለ ተናገሩ ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የBRICS አባል ሐገራት የአሜሪካዉን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለዩናይትድ ስቴትስ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ለማድረግ ዛቱ።
የጀርመን ወግ አጥባቂ እሕትማማች ፓርቲዎች የክርስቲያን ዴሞክራት ሕብረት (CDU)ና የክርስቲያን ሶሻል ሕብረት (CSU) አዲስ ያረቀቁት ስደተኞችን የሚያግድ ሕግ የሐገሪቱን ፖለቲከኞች እያሟገተ ነው።