ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የበረታውን ውጥረት ለመፍታት “የሰከኑ ውይይቶች” እንደሚያስፈልጉ አሳሰበች። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በመጪው ግንቦት በሚካሔደው ሀገራዊ ምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት “የሽብር ድርጊት” ሊባል እንደሚችል የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ። በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢዝላማባድ በአንድ መስጂድ ውስጥ አጥፍቶ ጠፊ በፈጸመው ጥቃት 31 ሰዎች ሲገደሉ ከ170 በላይ ቆሰሉ።
የሩሲያ ጦር ሠራዊት የወታደራዊ ሥለላ ምክትል ኃላፊ በሞስኮ በጥይት ተመተው ቆሰሉ።