• ኤርትራ በአስቸኳይ ሰራዊቷን ከሉአላዊ ግዛቶቿ እንድታስወጣ ኢትዮጵያ አሳሰበች። • በሰሜናዊ ናይጄሪያ ካዱና ግዛት ታጣቂዎች በአንድ የኃይማኖት አባት መኖሪያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ። • ደቡብ አፍሪቃ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ልታስወጣ ነው። • አሜሪካ በትውልድ ሃገራቸው መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ በማሴር የጦር መሣሪያ ሲያዘዋውሩ ደርሼባቸዋለሁ ያለችውን ደቡብ ሱዳናዊ በእስራት ቀጣች። • በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረሱ ስምምነቶች ዋጋ አይኖራቸውም ሲሉ አንድ የእስራኤል ሚንስትር ተናገሩ ።